ፖሊስ ዜና

ለጥቁር ገበያ ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ ነዳጅ እና ግምቱ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ከህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ መያዙን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

1Capture 6በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው በተለምዶ 7ኛ ሸንኮራ በረንዳ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ከሚገኘው «ትዕግስት ብሩክ ቶታል ማደያ»ውስጥ ጥር 12 ቀን 2011 ዓ/ም የተቋሙ ሰራተኞች ከህገ-ወጦች ጋር በመተባበር በ44 ጀሪካን 995 ሊትር ቤንዚን ከማደያው በመቅዳት ላይ እንዳሉ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የተቀዳውን ቤንዚን እና ሌላ ሊቀዳበት የነበረ 44 ባዶ ጀሪካን እንዲሁም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 29642 አይሱዙ ተሽከርካሪን ከአምስት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ ገልፃዋል፡፡

የማደያው ሰራተኞች ቤንዚን በጥቁር ገበያ ከሚሸጡ ህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ድርጊቱን መፈፀማቸውን ፖሊስ በምርመራው ማረጋገጡን ፤ በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ ተሳትፎ ያደረጉ አምስት ግለሰቦች ምርመራ እየተጠራባቸው እንደሚገኝ ኮማንደር ጌታነህ አስረድተዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ቤንዚን ከ11 ሺ ብር በላይ ዋጋ እንደሚያወጣ ኃላፊው ተናግረው በልዩ ልዩ ጊዜያት ግምቱ 38 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ 112 ጀሪካን ቤንዚን ተይዞ ምርመራው ተጣርቶ የምርመራ መዝገቡ ለዓቃቤ ህግ መላኩን ከኮማንደሩ ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም ልዩ ቦታው አማኑኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ ኮድ 3-47453 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከላይ ሲሚንቶ በማድረግ ከስር 63 ጀሪካን ቤንዚን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በድንገተኛ ፍተሻ መያዙን ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡  

በተያያዘ ዜና ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም ምዕራብ ሆቴል አከባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 80502 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ በኮንትሮ ባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ልዩ ልዩ እቃዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ ፖሊስ መምሪያው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተሽከርካሪውን መያዙን ነገር ግን አሽከርካሪውን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆንን ኮማንደር ጌታነህ ገልፃዋል፡፡Capture 8

ተሽከርካሪው በብርቱ ክትትል ሲያዝ በርከታ ጣቃ ጨርቆች ፣ 2ሺ የሞባይል ቻርጀሮች ፣ 3480 አይነቱ «ኑር ሴላ»የሆነ ሲጋራ እና 1ሺ የሪሲቨር ሪሞት ኮንትሮል ይዞ ለማለጥ ሲሞክር እንደተያዘ ሀላፊው አስረድተዋል፡፡

መርካቶ የንግድ ስፍራ በመሆኑ በተለይ የኮንትሮ ባንድ ንግድ እንደሚስተዋል እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቤንዚን በጥቁር ገበያ ለመሸጥ እንቅስቃሴ መኖሩን ነገር ግን ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሚሰጠው ጥቆማ አብዛኞቹ እየተያዙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ህገ-ወጥነትን በጋራ መከላከል የሚቻለው ህዝብና ፖሊስ በጋራ ሲጣመሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልፆ ህዝቡ ጥቆማ በመስጠትና አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ምስክር በመሆን እያረገ ያለውን የነቃ ተሳትፎ አጠናከሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ኮሚሽኑ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡Capture 2Capture 16 - CopyCapture 4Capture 13

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ በልዩ ልዩ ሙያ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ አመራሮች አስመረቀ፡፡ ከተመራቂዎቹ 57ቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ናቸው፡፡ በምረቃው ላይ የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተደረገ ባለው ጥረት ፖሊስ ኃላፊነቱን በብቃት ሊወጣ እንደሚገባ መልእክት ተላፏል፡፡EPUC
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ታህሳስ 27 ቀን 2011 ዓ/ም በፖሊስ ሳይንስ ፣ በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራ ፣ በፖሊስ ማናጅመንት እና በጤና የትምህርት ዘርፎች በድግሪ እንደዚሁም በወንጀል ምረመራ ዲፕሎም እና በጤና ደረጃ 2 በአጠቃለይ 481 አመራሮችን አስመርቋል፡፡ 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ክብርት ሙፈሪያት ካሚል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ ክቡር አቶ እንደሻው ጣሳው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፖሊስ አመራሮች በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል፡፡EPUC1
የተረጋጋ ኢኮኖሚ እና ፖሊቲካ ሂደት ለማስፈን በጥቅሉ የሰከነ ተውልድ ለመገንባታ በእውቀት ፣ በክህሎት እና በአመላካከለቱ የጠነከረ የፖሊስ አመራርና ባለሙያ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ክብርት ፕሬዝዳንቷ ባደረጉት ንግግር ገልፀው ፖሊሶች ተልዕኳቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡አንድ ፖሊስ በተላበሰው መልካም ስብእና እንደሚለካ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታውሰው ፖሊሶች ከራስ ይልቅ ለህብረተሰብ ጥቅም ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ተመራቂዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ 
የፖሊስ ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ም/ኮሚሽነር ጀኔራል ቀናዓ ያደታ በበኩላቸው ኮሌጁ ከተቋቋመበት 72 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ የትምህርት ተቋም መሆኑን አስታውሰው በእነዚህ ዓመታት ዩንቨርስቲ ኮሌጁ በርካታ የፖሊስ አመራሮችን ማፍራቱን ተናግረው ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በአደረጃጀት ፣ በአሰራር ፣ በሰው ኃይል እና በቴክኖሎጂ ራሱን ለማደረጃት እንዲሁም የመምህራንን የማስተማር ዘዴ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ማለቂያ እንደሌለው የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ገልፀው ተመራቂዎች ከኮሌጁ ያገኙትን እውቀት በተግባር ከሚያገኙት ልምድ ጋር በማጣመር ህዝባዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በቆይታቸው ወቅት በርከታ እውቀቶችን መገበየታቸውን ያነጋገርናቸው ተመራቂ አመራሮች ተናግረው በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የጀመረችውን ለውጥ ስኬታማ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡EPUC3
ከአጠቃላይ ተመራቂዎች መካከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፡-
• በጀረኒክ የመጀመሪያ ድግሪ -25
• በመደበኛ ዲፕሎማ 41ኛ ዙር -12
• በወንጀል ምርመራ ዲፕሎማ- 10
• በድህረ ምረቃ ዲፕሎማ 8ኛ ዙር -4
• በስፔሻል ድግሪ 6 በድምሩ 57 አመራሮችን አስመርቋል፡፡ ለተመራቂ አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእንኳን ደስያላችሁ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡EPUC4EPUC8

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከጀስቲስ ፎር ኦል-ፒኤፍ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር በሰብአዊ መብት ዙሪያ በአዳማ ከተማ ለኮሚሽኑ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስለጠና ሠጠ፡፡ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ

ታህሳስ 11 እስከ 13 ቀን 2011 ዓ.ም   በአዳማ ከተማ በተሰጠው ስልጠና ላይ ተገኝተው የስራ መመሪያ የሰጡት ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ እንደገለፁት በሀገራችንም ሆነ በተቋማችን የተጀመረውን የለውጥ ሂደት ለመስቀጠል ማህበረስቡ በየደረጃው የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች በፍጥነት ከመመለስ አንፃር ሳይንሳዊ በሆነ የአመራር ክህሎት በመታገዝ ሰዎች በተፈጥሮ ያገኙትን ሰብአዊ መብታቸውን በማንኛውም ሁኔታ እንዲከበር ለማድረግ ከስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ ተጠቅመው ለለውጡ መሳካት የአመራርንት ሚናቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡ ኮሚሽኑ ከመቼውም ጊዜ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑን ም/ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል፡፡km mekonen

የኮሚሽኑ ፖሊስ አካዳሚ ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር መኮንን አሻግሬ በበኩላቸው የፖሊስ ተቋም አመራሮችና አባለት ሰብአዊ መብትን አክብሮ የማስከበር ድርብ ኃላፊነት እንዳለባቸው አስታውሰው በተወሰ መልኩ በፀጥታ ኃይሉ የሚስተዋሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ለመከላከል ስልጠናው ለአመራሩ ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር ስለታመበት መዘጋጀቱን ገልፀዋል፡፡

የፖሊስ አመራር ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በቅድሚያ ጥሰቶቹን አስቀድሞ መከላከል ይገባል፡፡ ጥሰቶች ተፈፅመው ሲገኙ በፍጥነት ለህግ በማቅረብ ረገድ ፖሊስ ህገ መንግስቱንና በስሩያሉትን ህጎች መሰረት አድርጎ የሚሰራ ተቋም እንደመሆኑ መጠን ሰባአዊ መብቶችን አስቀድሞ ከማስከበር በተጨማሪ የማስከበር ግዴታውን በአግባቡ መወጣት እንዳለበት ስልጠናውን የሰጡት ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ ገልፀዋል ፡፡Docter  sisay

ለአመራሮቹ ስልታዊ የአመራር ዘዴዎች በተመለከተ እንደተቋም የለውጥ ግለቱን ለማስቀጠል አመራሩ ዘመኑ የሚጠይቀውን ሳይንሳዊ የአመራር ጥበብን በመጠቀም ቀልጣፋና ተደራሽ በየትኛውም ሁኔታ ለህግ የበላይነት ተገዥ የሆነ ቨመራር መኖር እንዳለበት ረ/ፕሮፌሰር ቴዎድሮስ ተሾመ ገልፀዋል፡፡hall

ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ሊዘዋወር የነበረ ጥይት በሕብረተሰቡ ጥቆማ ከእነ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡

ጥይቱ የተያዘው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ክልል ልዩ ቦታዉ አየር ጤና አውቶቢስ ተራ መናሃሪያ ግቢ ዉስጥ ነዉ፡፡

አንድ ግለሰብ ብዛቱ 394 ጥይት በመዳበሪያ ጠቅልሎ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ከተሞች ይዞ ለመሄድ ሲሞክር አየር ጤና መናኸሪያ ውሰጥ በአሽከርካሪው እና በረዳቱ በተደረገ ፍተሻ ተጠርጣሪው ከእነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡bullet

በአሁን ወቅት በሃገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች እየተስተዋለ የመጣዉን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ከመከላከል በተጨማሪ ሊያስከትል የሚችለዉን ጉዳት በመረዳት ህ/ሰቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን እያደረገ ያለዉን ጥረት  አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ 

በርበሬነው በማለት የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጠራባቸው ነው፡፡ መሰል ወንጀሎችን በመከላከል ዙሪያ የመናኸሪያ ሰራተኞ እያደረጉት ያለው አስተዋዕፆ ሊበረታታ ይገባል ተብሏል፡፡

kash vs berbereበወንጀሉን የተጠረጡት ግለሰቦች ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ለሊት ከንጋቱ 11፡30 ሠዓት ላይ የተለያዩ  የጦር መሳሪያዎችን በርበሬ ነው በማለት በሁለት ማዳበሪያዎች ውስጥ አድረገው በህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ ለማስጫን ሲሞክሩ  በጫኝና አውራጅ ስራ ላይ የተሰማሩ ተጠራጥረው ባደረጉት ፍተሻ መሳሪያዎቹን ከነተጠርጣዎቹ ይዘው ለፖሊስ ማስረከባቸውን ከአዲስ ፖሊስ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተው እያንዳንዱ ሰው ለሀገሩ ሰላም ሲል አስፈላጊውን ትብብር ሊያርግ ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡klash

የጉዳዩ መርማሪ ም/ ሳጅን ዳኛቸው ለገሰ እንደተናገሩት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ክልል በሚገኘው ትልቁ መናኸሪያ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በተደጋጋሚ ጊዜ ተመሳሳይ ወንጀሎች እንደሚፈፀም አስታውሰው በአውቶቢስ ተራው ውስጥ  በጫኚና አውራጅ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች  በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተሰማሩ ግለሰቦችን በተደጋጋሚ ጊዜ እጅ ከፍንጅ ይዘው ለፖሊስ ማስረከባቸው የሚበረተታ ስለሆነ ተግባሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡   

አንዳንድ ግለሰቦች ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ፖሊስ ገለፀ፡፡ ሰልፉ በከተማው አስተዳደር ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ ስፍራዎች ከፀጥታ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እንዲሁም የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ ታህሳስ 6 እና እሁድ ታህሳስ 7/2011 ዓ/ም አንዳንድ ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩም ይሁን በፖሊስ እውቅና የሌለው መሆኑን የኮሚሽኑ ኢንዶክተሪኔሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ከላከው ዜና መረዳት ተችሏል፡፡logo

ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ-መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሞ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑን ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑመልእክቱን አስተላፏል፡፡

በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

በዓለም አቀፍ 31 በሀገር አቀፍ 30 ጊዜ የተከበረውን የኤች.አይ. ኤድስ ቀን ምክንያት በማድረግ ለፖሊስ አመራሮችና አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ፡፡hivday1

የስልጠናው ተከፋዩች በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የደም ልገሳ እና የኤች.አይ. ምርመራ አደረጉ፡፡ "ለኤች.አይ. ኤድስ ይበልጥ ተጋላጭ ነን፣ እንመርመር እራሳችን እንወቅ" በሚል መሪ ቃል ህዳር 28 ቀን 2011 . በኮሚሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማሥጨበጫ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ጤንነቱ የተጠበቀ የህዝብ አገልጋይ የፖሊስ አባላት እንዲኖር ኮሚሽኑ አበክሮ እንደሚሰራ ገልፀው ሁሉም አመራርና አባላት ከተላላፊ በሽታዎች እራሳቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው መልእክት አሳስበዋል፡፡hivdat2

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች.አይ. ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር /ቤት ኃላፊ ሲስተር ብርዛፍ ገብሩ በበኩላቸው ኤች.አይ./ ኤድስ በሀገራችን በርካታ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶችን እያስከተለ መሆኑን አስታውሰው በተለይ ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል በቫይረሱ እየተጠቃ ስለሆነ ስርጭቱን ለመግታትና ለመቆጣጠር ሁሉም ዜጋ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ሲሉ የበሽታው ሰለባ መክረዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው ሀብት ልማት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ኮሚሽነር ዮሐንስ ጭልጆ አብዛኛው የኮሚሽኑ አባላት በወጣትነት የዕድሜ ክልል የሚገኙ በመሆናቸው ራሳቸውንና ሌሎችን ከኤች. አይ. ኤድስ በመከላከል ሀላፊነታቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል ብለው ኮሚሽኑ ከአዲስ አበባ የኤች አይ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር /ቤት ጋር ያለውን ቁርኝት አጠናክሮ በመቀጠል መሰል የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

ማዕከልን ጨምሮ ከአስሩ /ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለተውጣጡ አመራርና አባላት በቅድመ መከላከል ዙሪያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤች.አይ. ኤድስ መከላከል እና መቆጣጠር /ቤት ባለሙያ በሆኑት ሲስተር ሽብሬ መንገሻ አማካኝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በሌላ መልኩ የፖሊስ አመራር እና አባላቱ በደም እጦት ምክንያት ወገኖቻችን ህይወቻችን እንዳያጡ ለኢትዮጵያ ደም ባንክ አገልግሎት ደም የለገሱ ሲሆን በፍቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የኤች.አይ./ኤድስ ምርመራ አድርገዋል፡፡hivday5hivday4

የጀርመን ፖሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡ የጀርመን ፖሊስ ለኮሚሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጾል፡፡

ህዳር 25ቀን 2011 ዓ.ም የጀርመን ፖሊስ ምክትል ፕሬዝዳንት ዩርገን ሹበርት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡jer 1

በውይይቱ ላይ ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር በእድገቷ ከፍተኛ ደረጃ ላይ ከምትገኘው የጀርመን ሀገር ፖሊስ የሀገራችን የፖሊስ ተቋማት በርካታ መልካም ተሞክሮዎችን መቅሰም እንደለባቸው ተናግረው የሁለቱ ሀገራት ፖሊሶች የቀደመ ግንኙነት እንዳላቸው እና ጀርመን የኢትዮጵያን ፖሊስ ለማጠናከር ልዩ ልዩ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን በማስታዎስ አሁንም ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡  jer 2

የጀርመን ፌደራል ፖሊስ ምክትል ፕሬዚዳንት ዩርገን ሹበርት በበኩላቸው ኢትዮጵያ በለውጥ ጉዳና ላይ መሆኗን መረጃ እንደላቸው ገልፀው የሀገሪቷን የፖሊስ አቅም ለማጎልበት እና ተባብረው መስራት በሚያስችልበት ጉዳይ ዙሪያ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያን ፖሊስ አቅምን ለማጎልበት በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች የበኩላቸውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡jer 3

ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሊገባ የነበረው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሱሉልታ ኬላ ላይ በአዲስ አባበ ፖሊስ በሻለቃ አራት የወንጀል መከላከል ተወርዋሪ ሃይል አባላት እና በብሄራዊ ደህንነት ሰራተኞች 9120(ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ሃያ ) የክላሽ ኮቭ ጥይት እና 39600 ብር (ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ)ብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡bullet

ህገ ወጥ የጦር  መሳሪያው እና ገንዘቡ ሊያዝ የቻለው በቅድመ ህብረተሰብ ጥቆማ አማካኝነት ነው፡፡ የከተማችን አዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈንና የህግ የበላይነትንለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከህብረተሰቡና ከሚመለከተቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እያደረገ ያለው የወንጀል መከላከል ተግባር የሚበረታታ ነው፡፡ በተለይ ሰፊው የህብረተስብ ክፍል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን አስቀድሞ በመጠቆም በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ ረገድ  ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡bulle mobullet 1

በአ/አበባ  ከተማ  የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ ፍሰቱን ለማሳለጥ የሚያግዙ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን  አስታወቀ፡፡

በከተማችን አ/አበባ በተለያዩ ቦታዎች ላይ ዘወትር የሚታየው የትራፊክ መጨናነቅ አሽከርካሪውና የመንገድ ተጠቃሚው ባቀደው ሰዓት ጉዳዩን እንዳይፈፅም ምክንያት እየሆነ መምጣቱ የሚታወቅ ነው፡፡ በተለይም ዋና ዋና በሚባሉ የከተማው መንገዶች ላይ በሥራ መግቢያ እና መውጫ ሰዓታት ችግሩ ጎልቶ የሚታይ ነው፡፡2

            የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከከተማው መንገድ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ ጋር በመቀናጀት የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው በተመረጡ ቦታዎች ላይ ፍሰቱን የማሳለጥ ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ህዳር 18 ቀን 2011 ዓ.ም የኮሚሽኑ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከል ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ በጽ/ቤታቸው በሰጡት መግለጫ ፍሰቱ ከሚበዛባቸው መንገዶች ውስጥ አንዱ በሆነው በሀያት መገናኛ መስመር ላይ ከህዳር 17 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ ፍሰቱን ሠላማዊ የማድረግ ተግባር ተጀምሯል፡፡1

አንዳንድ አሽከርካሪዎች በሰጡት አስተያየት የትራፊክ መጨናነቁን ለማሳለጥ በጊዚያዊነት የተሰራው ስራ ሊበረታታ የሚገባው ቢሆንም በዘላቂነት መፍትሄ የሚያሻው ጉዳይ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

እንደ ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ገለፃ የከተማው አስተዳደር ለረጅም ዓመታት ያለምንም ልማት ታጥረው የተቀመጡ  ቦታዎችን ወደ ልማት እንዲገቡ ቅድመ ዝግጅት  እያደረገ መሆኑን ገልፀው በተወሰኑ ቦታዎች ላይ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎችን በማዘጋጀት ዘለቄታነት ያለው ሠላማዊ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ  አብራርተው የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ፍሰቱን ቀልጣፋ ለማድረግ በሚሰራው ስራ ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡  34


Warning: count(): Parameter must be an array or an object that implements Countable in /data/var/www/vhosts/addispolice.gov.et/httpdocs/templates/leo_news/html/com_k2/default/category.php on line 257
Page 2 of 3

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus