የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ በልዩ ልዩ ሙያ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ አመራሮች አስመረቀ፡፡

Wednesday, 09 January 2019 08:42

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ በልዩ ልዩ ሙያ ያሰለጠናቸውን የፖሊስ አመራሮች አስመረቀ፡፡ ከተመራቂዎቹ 57ቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች ናቸው፡፡ በምረቃው ላይ የተረጋጋ ማህበረሰብ ለመፍጠር እየተደረገ ባለው ጥረት ፖሊስ ኃላፊነቱን በብቃት ሊወጣ እንደሚገባ መልእክት ተላፏል፡፡EPUC
የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩንቨርስቲ ኮሌጅ ታህሳስ 27 ቀን 2011 ዓ/ም በፖሊስ ሳይንስ ፣ በወንጀል መከላከል፣ በወንጀል ምርመራ ፣ በፖሊስ ማናጅመንት እና በጤና የትምህርት ዘርፎች በድግሪ እንደዚሁም በወንጀል ምረመራ ዲፕሎም እና በጤና ደረጃ 2 በአጠቃለይ 481 አመራሮችን አስመርቋል፡፡ 
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕሬዝዳንት ክብርት ሳህለወርቅ ዘውዴ ፣ ክብርት ሙፈሪያት ካሚል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ፣ ክቡር አቶ እንደሻው ጣሳው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጀኔራል እና ሌሎች የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የፖሊስ አመራሮች በምረቃ ፕሮግራሙ ላይ ተገኝተዋል፡፡EPUC1
የተረጋጋ ኢኮኖሚ እና ፖሊቲካ ሂደት ለማስፈን በጥቅሉ የሰከነ ተውልድ ለመገንባታ በእውቀት ፣ በክህሎት እና በአመላካከለቱ የጠነከረ የፖሊስ አመራርና ባለሙያ ማፍራት እንደሚያስፈልግ ክብርት ፕሬዝዳንቷ ባደረጉት ንግግር ገልፀው ፖሊሶች ተልዕኳቸውን ለመወጣት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡አንድ ፖሊስ በተላበሰው መልካም ስብእና እንደሚለካ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ አስታውሰው ፖሊሶች ከራስ ይልቅ ለህብረተሰብ ጥቅም ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ ተመራቂዎችን እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡ 
የፖሊስ ዮኒቨርስቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ም/ኮሚሽነር ጀኔራል ቀናዓ ያደታ በበኩላቸው ኮሌጁ ከተቋቋመበት 72 ዓመታትን ያስቆጠረ አንጋፋ የትምህርት ተቋም መሆኑን አስታውሰው በእነዚህ ዓመታት ዩንቨርስቲ ኮሌጁ በርካታ የፖሊስ አመራሮችን ማፍራቱን ተናግረው ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት በአደረጃጀት ፣ በአሰራር ፣ በሰው ኃይል እና በቴክኖሎጂ ራሱን ለማደረጃት እንዲሁም የመምህራንን የማስተማር ዘዴ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ትምህርት ማለቂያ እንደሌለው የኮሌጁ ፕሬዝዳንት ገልፀው ተመራቂዎች ከኮሌጁ ያገኙትን እውቀት በተግባር ከሚያገኙት ልምድ ጋር በማጣመር ህዝባዊ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በቆይታቸው ወቅት በርከታ እውቀቶችን መገበየታቸውን ያነጋገርናቸው ተመራቂ አመራሮች ተናግረው በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የጀመረችውን ለውጥ ስኬታማ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን በብቃት ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡EPUC3
ከአጠቃላይ ተመራቂዎች መካከል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፡-
• በጀረኒክ የመጀመሪያ ድግሪ -25
• በመደበኛ ዲፕሎማ 41ኛ ዙር -12
• በወንጀል ምርመራ ዲፕሎማ- 10
• በድህረ ምረቃ ዲፕሎማ 8ኛ ዙር -4
• በስፔሻል ድግሪ 6 በድምሩ 57 አመራሮችን አስመርቋል፡፡ ለተመራቂ አመራሮች የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የእንኳን ደስያላችሁ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡EPUC4EPUC8

Rate this item
(2 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus