አገልግሎታችን


 የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን

        የዜጎች ቻርተር፡-

$11.  መግቢያ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 12/1 ላይ እንደተመለከተው የመንግስት አሠራር ለሕዝብ ግልፅ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት ይላል፡፡ በዚሁ መሰረት፡-

የመንግስት አሠራር በግልፅና ተጠያቂነት ያለው ለማድረግ የመንግስት ተቋማት ለዜጎች /ሕዝቦች የሚሠጧቸውን አገልግሎቶች የሚያስታውቅበትን አሠራር እየለየ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ አሠራሮች አንዱ የመንግስት ተቋማት የዜጎች ቻርተር ቴምፕሌት አዘጋጅተው ተገልጋዩ ሕዝቦች እንዲያውቁ ማድረግ ሲሆን መንግስት በአገር አቀፍ ደረጃ እንዲተገበር ባወጣው መመሪያ መሠረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለዜጎች የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች የሚሰጡበትን ሁኔታ ግልፅ በሆነ መንገድ ለማከናወን የዜጎች ቻርትር በማዘጋጀት ከህዝብ፤ከሚመለከታቸው አካላትና ከመ/ቤቱ ሠራተኞች ጋር ውይይት በማድረግ አፀድቆ በስራ ላይ ማዋሉ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት የተዘጋጀው ቻርተር ማሻሻል በማስፈለጉ ተገቢ ማሻሻያዎችን በመጨመር ይህንን ቻርተር በድጋሚ አዘጋጅቷል፡፡

$12.  የተቋሙ ራዕይ፡-

ከተማችን አዲስ አበባ ሠላምና ደህንነት የሰፈነባትና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠበት ከተማ ሆኖ ማየት፣

$13.  ተልዕኮ፡-

  የሀገሪቱን ሕገ መንግስትና ሕገ መንግስቱን ተከትለው የሚወጡ ሌሎች ህጎችን አክብሮ በማስከበርና የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ ወንጀልና የትራፊክ አደጋን በመከላከል፤ተፈሞ ሲገኝ በህግ አግባብ አጣርቶ አጥፊዎች ተገቢውን የሕግ ውሳኔ እንዲያገኙ በማድረግ የከተማውን ህብረተሰብ ሠላምና ደህንነት ማረጋገጥ፣

$14.  የኮሚሽኑ እሴቶች፡-

$11.  ለኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት ታማኝ መሆን፣

$12.  ከራስ በላይ የሀገርንና የህዝብን  ጥቅም ማስቀደም፣

$13.  የተስተካከለ ፖሊሳዊ ስብዕና፤  

$14.  በማንኛውም ፖሊሳዊ ተልዕኮ የላቀ ውጤት፣

$15.  የቻርተሩ ዓላማ፡-

$11.  የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ፣

$12.  ለዜጎች በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት አገልግሎት ለመስጠት፣

$13.  ተቋሙ ለሚያገለግው ሕዝብ ተጠያቂነትን በግልፅ ለማመላከት፣

$14.  ዜጎች ከተቋሙ ምን ዓይነት አገልግሎት በምን አይነት የጥራት፤የጊዜ፤የመጠን፤የወጨ ደረጃ ማግኘት እንደሚገባቸው ለማሳወቅ፣

$15.  ዜጎች በተቋሙፖሊሳዊ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት ጥቆማና ግብዓት የሚሰጡበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣

 ዝርዝር የዜጎች ቻርተር

 

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus