Warning: count(): Parameter must be an array or an object that implements Countable in /data/var/www/vhosts/addispolice.gov.et/httpdocs/components/com_k2/models/item.php on line 877

ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ ነዳጅ እና ግምቱ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ከህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ ተያዘ

Wednesday, 23 January 2019 11:47

Warning: count(): Parameter must be an array or an object that implements Countable in /data/var/www/vhosts/addispolice.gov.et/httpdocs/templates/leo_news/html/com_k2/default/item.php on line 219

ለጥቁር ገበያ ለሽያጭ ሊቀርብ የነበረ ነዳጅ እና ግምቱ ከ1ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጣ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ከህብረተሰብ በደረሰ ጥቆማ መያዙን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

1Capture 6በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው በተለምዶ 7ኛ ሸንኮራ በረንዳ ተብሎ ከሚጠራ አካባቢ ከሚገኘው «ትዕግስት ብሩክ ቶታል ማደያ»ውስጥ ጥር 12 ቀን 2011 ዓ/ም የተቋሙ ሰራተኞች ከህገ-ወጦች ጋር በመተባበር በ44 ጀሪካን 995 ሊትር ቤንዚን ከማደያው በመቅዳት ላይ እንዳሉ የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የተቀዳውን ቤንዚን እና ሌላ ሊቀዳበት የነበረ 44 ባዶ ጀሪካን እንዲሁም የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3 አ/አ 29642 አይሱዙ ተሽከርካሪን ከአምስት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዲቪዚዮን ኃላፊ ኮማንደር ጌታነህ በቀለ ገልፃዋል፡፡

የማደያው ሰራተኞች ቤንዚን በጥቁር ገበያ ከሚሸጡ ህገ-ወጦች ጋር በመተባበር ድርጊቱን መፈፀማቸውን ፖሊስ በምርመራው ማረጋገጡን ፤ በህገ-ወጥ ተግባሩ ላይ ተሳትፎ ያደረጉ አምስት ግለሰቦች ምርመራ እየተጠራባቸው እንደሚገኝ ኮማንደር ጌታነህ አስረድተዋል፡፡

በቁጥጥር ስር የዋለው ቤንዚን ከ11 ሺ ብር በላይ ዋጋ እንደሚያወጣ ኃላፊው ተናግረው በልዩ ልዩ ጊዜያት ግምቱ 38 ሺ ብር በላይ የሚያወጣ 112 ጀሪካን ቤንዚን ተይዞ ምርመራው ተጣርቶ የምርመራ መዝገቡ ለዓቃቤ ህግ መላኩን ከኮማንደሩ ገለፃ መረዳት ተችሏል፡፡ ከዚህ ቀደም ታህሳስ 8 ቀን 2011 ዓ/ም ልዩ ቦታው አማኑኤል ቤተ-ክርስቲያ አካባቢ ኮድ 3-47453 አ/አ የሆነ አይሱዙ ተሽከርካሪ ከላይ ሲሚንቶ በማድረግ ከስር 63 ጀሪካን ቤንዚን ጭኖ ሲንቀሳቀስ በድንገተኛ ፍተሻ መያዙን ኮማንደሩ አስረድተዋል፡፡  

በተያያዘ ዜና ጥር 13 ቀን 2011 ዓ/ም ምዕራብ ሆቴል አከባቢ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 80502 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ግምቱ ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ በኮንትሮ ባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ልዩ ልዩ እቃዎች ይዞ ሲንቀሳቀስ ፖሊስ መምሪያው ከህዝብ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ተሽከርካሪውን መያዙን ነገር ግን አሽከርካሪውን ለመያዝ ክትትል እየተደረገ መሆንን ኮማንደር ጌታነህ ገልፃዋል፡፡Capture 8

ተሽከርካሪው በብርቱ ክትትል ሲያዝ በርከታ ጣቃ ጨርቆች ፣ 2ሺ የሞባይል ቻርጀሮች ፣ 3480 አይነቱ «ኑር ሴላ»የሆነ ሲጋራ እና 1ሺ የሪሲቨር ሪሞት ኮንትሮል ይዞ ለማለጥ ሲሞክር እንደተያዘ ሀላፊው አስረድተዋል፡፡

መርካቶ የንግድ ስፍራ በመሆኑ በተለይ የኮንትሮ ባንድ ንግድ እንደሚስተዋል እንዲሁም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ቤንዚን በጥቁር ገበያ ለመሸጥ እንቅስቃሴ መኖሩን ነገር ግን ህብረተሰቡ ለፖሊስ በሚሰጠው ጥቆማ አብዛኞቹ እየተያዙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ህገ-ወጥነትን በጋራ መከላከል የሚቻለው ህዝብና ፖሊስ በጋራ ሲጣመሩ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልፆ ህዝቡ ጥቆማ በመስጠትና አጥፊዎች በህግ እንዲጠየቁ ምስክር በመሆን እያረገ ያለውን የነቃ ተሳትፎ አጠናከሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ኮሚሽኑ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡Capture 2Capture 16 - CopyCapture 4Capture 13

Last modified on Wednesday, 23 January 2019 12:02
Rate this item
(3 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.


Notice: Only variables should be assigned by reference in /data/var/www/vhosts/addispolice.gov.et/httpdocs/templates/leo_news/html/com_k2/default/item.php on line 656

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus