ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድግ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ ያገኘውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

Tuesday, 17 June 2025 07:46
ህጋዊ የንግድ ፈቃድን ሽፋን በማድግ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ ያገኘውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 6 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ሀሰተኛ ሰነድ ሲያዘጋጅ እጅ ከፍንጅ የተያዘው ጸሎት ይስማው ምግባሩ የተባለው ግለሰብ የህትመት ስራን ለመስራት በሚያስችል የንግድ ፈቃድ ሽፋን በማድረግ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አየር ጤና አካባቢ በሚገኘው ህትመት ቤቱ ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን በማዘጋጀት ላይ እያለ ግንቦት 27 ቀን 2017 ዓ/ም እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡
ህጋዊ የህትመት ቤትን እንደሽፋን በመጠቀም ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች፣ መታወቂያዎች፣ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ፣ የባንክ ደብተር፣ በዋነኝነት የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት የቤተሰብ ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መታወቂያ በማዘጋጀት ለግለሰቦች ከ400 እስከ 3000 ብር ሲሸጥ እንደነበር በምርመራ መረጋገጡ በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ክፍል ገልጿል፡፡
ተጠርጣሪውና ግብር አበሮቹ ሀሰተኛ ሰነድ ለማዘጋጀት የሚጠቀሙባቸውን ማህተም መቅረጫ ማሽን፣ ላፕቶፕ፣ ፕሪንተሮች እንዲሁም የተለያዩ ተቋማት ማህተሞችና ቲተሮች፣ የአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ የቤተሰብ ነፃ ግልጋሎት መታወቂያ እና የተለያዩ የትምህርት ማስረጃዎችን መያዙን ፖሊስ አሰታውቋል፡፡
በወንጀሉ ተጠርጥሮ የተያዘው ግለሰብ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ የከተማ አውቶቡስ አገልግሎት ድርጅት ሲሰራ የነበር እና በስነ-ምግባር ችግር ከተቋሙ መባረሩን ፖሊስ ጨምሮ ገልጿል፡፡
 
ያልተገባ ጥቅምን ለማግኘት ሀሰተኛ ሰነድ ማዘጋጀትም ሆነ መጠቀም የህግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል ህገ ወጥ ተግባር በመሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ሀሰተኛ ሰነድ በሚያዘጋጁና በሚጠቀሙ ላይ እያደረገ ያለውን ቁጥጥር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ:- ኢንስፔክተር እመቤት ሃብታሙ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
Last modified on Tuesday, 17 June 2025 07:59
Rate this item
(0 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus