በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚፈጠሩ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከል ለአዲስ አ አበባ ከተማ ሠላም መስፈን ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ፤ በጉዳዩ ዙርያ ከጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት ሰብሳቢዎች እና ከፖሊስ አካላት ጋር ስልጠናዊ ውይይት ተካሄዷል።

Friday, 13 June 2025 11:30
በጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ የሚፈጠሩ ግጭቶችን አስቀድሞ መከላከል ለአዲስ አ አበባ ከተማ ሠላም መስፈን ጉልህ ሚና እንዳለው ተገለፀ፤ በጉዳዩ ዙርያ ከጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት ሰብሳቢዎች እና ከፖሊስ አካላት ጋር ስልጠናዊ ውይይት ተካሄዷል።
***
ስልጠናዊ ውይይቱ የተካሄደው ዛሬ ሰኔ 5 ቀን 2017 ዓ/ም በካንቲባ ፅ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው። በስልጠናዊ ውይይቱ ላይ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሠላም ሚኒስቴር የግጭት ጥናት ትንተና ዴስክ ኃላፊ የሆኑት አቶ ይትባረክ ተስፋዬ፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር አይናለም በየነ፣ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉነህ ፈይሳ፣ የሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ደንዲር፣ አባ ገዳዎች እና የጋሞ አባቶች ተገኝተዋል።
በግጭት አፈታት ዙሪያ ጥናታዊ ጽሑፍ ያቀረቡት አቶ ይትባረክ ተስፋዬ ዓላማው በግጭት ምክንያት የሚመጣውን ሁከት መከላከል እና መቀነስ ለማስቻል ነው ብለዋል፤ኃላፊው አክለውም የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ነዋሪውን ለግጭት የሚያነሳሱ የፍሳሽና የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣ የተለያዩ ስርቆቶች ስለሚኖሩ በዚህ ምክንያት የሚመጣው የነዋሪዎች ግጭት አላስፈላጊ የጸጥታ ችግር እንዳይፈጥር አስቀድሞ ለመከላከል ስልጠናው አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል።
በየክፍለ ከተማው ባሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች የሚኖሩ ዜጎች እንደሌሎች ነዋሪዎች ሁሉ የጸጥታ ችግር እንዳያጋጥማቸው እና ግጭቶች ሲፈጠሩም ወደ አልሆነ አቅጣጫ እንዳያመሩ በኦፊሰሮቻቸው አማካኝነት በቅርበት እንደሚሰራ የገለጹት ረ/ኮሚሽነር አይናለም በየነ ሲሆኑ ከዚህ ስልጠና በኋላ ደግሞ ከዚህ በተሻለ መልኩ መሰራት እንዳለበት ጠቅሰዋል።
የሠላም እና ጸጥታ ቢሮ ም/ኃላፊው አቶ ተስፋዬ ደንዲር በበኩላቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባባቶችን እና ግጭቶችን ለመፍታት ኮሚቴ ተዋቅሮ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በጋራ እየተሰራ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ይህንን ለማጠናከርም የዛሬው ስልጠና ወሳኝነት እንዳለው ተናግረዋል።
በስልጠናዊ ውይይቱ ላይ ተገኝተን ያነጋገርናቸው የስልጠናው ተሳታፊዎች ከዚህ ቀደም የግጭት መንስኤዎችን በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር እና ከነዋሪው ጋር እንደሚሰሩ ጠቁመው ስልጠናው ይህንን ለማጠናከር ያግዘናል በማለትም ጠቁመዋል።
ከመድረኩም ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄ እና አስተያየቶች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።
*
ዘገባ፦ ረ/ሳጅን መልካሙ ዜና
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
 
 
Last modified on Monday, 16 June 2025 16:37
Rate this item
(0 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus