ከሚጠብቁት ድርጅት የቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች ከነ አባሪዎቻቸው ተይዘው በ8 እና በ3 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

Thursday, 19 June 2025 06:47
ከሚጠብቁት ድርጅት የቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች ከነ አባሪዎቻቸው ተይዘው በ8 እና በ3 ዓመት ጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።
***
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 11 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ከዚህ ቀደም ተከሳሾቹ ወንጀሉን እንደፈፀሙ መያዛቸውን እና በምርመራ ሂደት እንደሚገኙ በገፃችን ያስተላለፍን መሆኑ ይታወቃል።
ተከሳሾቹ ወንጀሉን የፈፀሙት የካቲት 16 ቀን 2017 ዓ/ም በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ቅጥር ግቢ ከሚገኘው ቶም ቪዲዮ ግራፊና ፎቶ ግራፊ ማሰልጠኛ ተቋም በሌሊቱ ክ/ጊዜ ነው፡፡ ሁለቱ ተከሳሾች በፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቶም የቪዲዮ ግራፊና እና የፎቶ ግራፊ ማሰልጠኛ ውስጥ በጥበቃ ሰራተኝነት ተቀጥረው ይሰራሉ፡፡
ማስተዋል ገላና እና ሀብታሙ ታደሰ የተባሉ የማሠልጠኛ ትምህርት ቤቱ የጥበቃ ሠራተኞች መርክነህ ታንጋና ታደለ ማሩጫ ከተባሉ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የማሰልጠኛ ተቋሙን ዕቃ ግምጃ ቤት ሰብረው በመግባት ጠቅላላ ግምታቸው 2.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ 29 የፎቶ ግራፍ ካሜራዎች፣ 3 ቪድዮ ካሜራዎች፣ 2 ስፖት ላይቶች፣ 2 ማንዋል ላይቶች፣ የካሜራ ባትሪዎች፣ 10 የባትሪ ቻርጀሮች፣ 2 ኤልኢዲ ላይቶች፣ 4 የገመድ ማይኮች እንዲሁም የቻርጀር ማራዘሚያ በመስረቅና በተሽከርካሪ በመጫን የተወሰነውን እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኝ የማስተዋል ገላና ፎቶ ቤት ውስጥ ያስቀመጡ ሲሆን የቀረውን ደግሞ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ወላይታ ሶዶ ከተማ በመውሰድ በሌሎች የስራ ቦታቸው የደበቁና እንዲሸጥ ያደረጉ ሲሆን ፖሊስ ባከናወነው ጠንካራ የምርመራና የክትትል ስራ ተጠርጣሪዎቹን ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ይታወሳል።
ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ሶስተኛ ወንጀል ችሎት ማስተዋል ገላና ሀብታሙ ታደሰ በጥበቃ ሰራተኝነት ተቀጥረው የነበሩ እያንዳንዳቸው በ8 ዓመት ፅኑ እስራት ሲቀጡ በአባሪነት ተሳትፎ የነበራቸው መርክነህ ታንጋና ታደለ ማሩጫ እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፏል።
የትኛውም ተቋምም ሆነ ግለሰብ የሰራተኛ ቅጥር በሚፈፅምበት ወቅት ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ ያላቸውን መረጃዎች እና ዋስትና በተገቢው ሁኔታ ማጤን መሰል ወንጀሎች ለመፈጸም ዕድል እንዳይኖራቸው የሚያደርግ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ገልጿል።
*
ዘገባ፦ ረ/ሳጅን ፍሬወይኒ ገ/ጻዲቅ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
Rate this item
(0 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus