ፖሊስ ከጫኝና አውራጅ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ፤ ውይይቱ አንዳንድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡ *** አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ውይይቱ የተካሄደው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር አይናለም በየነ በተገኙበት በጠ Featured

Tuesday, 01 July 2025 10:47
ፖሊስ ከጫኝና አውራጅ ማህበራት ተወካዮች ጋር ውይይት አደረገ፤ ውይይቱ አንዳንድ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም የተዘጋጀ መሆኑ ተገልጿል፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ውይይቱ የተካሄደው ሰኔ 20 ቀን 2017 ዓ/ም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረዳት ኮሚሽነር አይናለም በየነ በተገኙበት በጠቅላይ መምሪያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነው።
ህብረተሰቡ ከጫኝና አውራጅ ጋር ተያይዞ የሚያነሳቸውን ቅሬታዎች ለማረም እና በሦስት ወራት ውስጥ በስራ ላይ የተስተዋሉ ክፍተቶችን ለማስተካከል እንዲሁም የተሰሩ መልካም ስራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ውይይት እንደሆነ ከመድረኩ መረዳት ተችሏል።
በውይይቱ ላይ ረዳት ኮሚሽነር አይናለም በየነ እንደገለፁት በጫኝ እና አውራጅ የስራ መደብ ላይ የተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚያገለግሉትን ማህበረሰብ ሳያንገላቱ በታማኝነት እና በቅንነት በህግ አግባብ ማገልግል እንዳለባቸው በመጥቅስ በሚሰሩበት ቀጠና ላይ ምንም ዓይነት ወንጀል እንዳይፈፀም ከፖሊስ ጋር ተቀናጅተው መሰራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፤ ይህ ሳይሆን ከቀረ የህግ ተጠያቂነት የሚያስከትል መሆኑን ኃላፊዋ ገልፀው ሁሉም ጫኝና አውራጅ ወንጀልን በመከላከል ሂደት ውስጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ሊያበርክት ይገባል ብለዋል፡፡
ያነጋገርናቸው የውይይቱ ተሳታፊዎች ውይይቱ ክፍተቶቻቸውን ያረሙበት እና ለጥያቄዎቻቸው መልስ ያገኙበትና ፍርያማ መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይም መሰል ውይይቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ከባለንብረት ፈቃድ ውጭ እቃ እናወርዳለን ወይም እንጭናለን በማለት የሚያስፈራሩና ጫና የሚፈጥሩ አካላትን ፖሊስ ፈፅሞ እንደማይታገስ አስታውቆ ህብረተሰቡ ከጫኝና አውራጅ ጋር ተያይዞ ችግር ከገጠመው በህብረተሰብ ተሳትፎ መተግበሪያ /Citizen Engagement/ ወይም 991 ነፃ የስልክ መስመር መረጃ ማድረስ እንደሚችል እና ፈጣን ምላሽ እንደሚያገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡
*
ዘገባ፦ ረ/ሳጅን ፍፁም በቀለ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”
Last modified on Tuesday, 01 July 2025 14:10
Rate this item
(0 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus