የኢ/ፌ/ፖ/ኮ/ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የፖሊስ ኮሚሽነሮች እና አመራሮች በተገኙበት አዲስ አበባ ስብሰባቸውን አካሂደዋል፡፡የውይይቱ አጀዳዎች መካከል የፖሊስ ሪፎረም፤የሰራዊቱ ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም፤ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የመሳሰሉት ሲሆ‹‹ህገ መንግስታዊ ተልዕኮአችንን በብቃት በመወጣት ለህግ የበላይነት መስፈን እንተጋለን›› በሚል መሪ ቃል በሰፊው ተወያይተውበታል፡፡
የፖሊስ ተቋማዊ ህዳሴ አንገብጋቢነት እና ወቅታዊነት ምን እንደሚመስል እና ተቋሙ ከሃገሪቱ እድገት ጋር የዘመነ ፖሊስን ለመፍጠር መታደስ እንዳለበትና ህዝብ የሚፈራው ሳይሆን ህዝብ የሚያከብረው ከወንጀለኛ ጋር የማይደራደር ፖሊስ ለመፍጠር የሚያስችል የመዋቅር /ሪፎርም/በመዘርጋት ዘመናዊ የፖሊስ ሃይል ማፍራት አለብን ብለዋል፡፡
ኮምሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጅማል እንደገለጹት የጠራና ግልጽ አሰራሮችን ለመከተልና ወደ ስራ ለመግባት በሰራዊቱ የደሞዝ፡የሬሽን፤የመኖሪያ ካምፕ እና ሌሎች ከኑሮ ሁኔታዎች ጋር የሚታዩ ቸግሮች በአፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጠው አጽኖት በመስጠት ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ኮሚሽነር ጀኔራሉ አየይዘው እደተናገሩት ከምንግዜውም በላይ በፖሊስ እና በጸጥታ ሃይሉ ማህበራዊ ሁኔታ በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው እነደሚሰሩና ሪፎርሙ አሰከ አባላት ድረስ የሚወረድ አደረጃጀት አንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
# Ethiopian Federal Police Commission - ህዝብ ግንኙነት
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቦክስ ቡድን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን የሚያዘጋጀውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልቦች ሻምፒዮና ውድድር ላይ ተካፋይ በመሆን አራት ዙር በሴት 6 የወርቅ፣ 3 የብር እና 6 ነሐስ በአጠቃላይ በ15 ሜዳሊያዎች 30 ነጥብ በማምጣት የዓመቱ አሸናፊ በመሆን ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ በተመሳሳይ በወንዶች ደግሞ በ38 ነጥብ የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
ሴት ሞተረኛ ትራፊክ …!
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ አደጋን በመከላከልና የትራፊክ ፍሰቱን ሊያሳልጡ የሚችሉ ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን የሞተረኛ ትራፊክ አባላት አስመርቋል፤ በስልጠናው ላይ 173 አባላትን ያካተተ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 16ቱ ሴቶች ሲሆኑ ኮሚሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ሞተኞችን እንዳስመረቀ ተነግሯል፤ ም/ኮሚሽነር ተስፋዬ ደንደና የመንገድ ትራፊክ አደጋን መከላከል ዋንኛ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
ሴት ሞተረኛ ትራፊክ …!
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ አደጋን በመከላከልና የትራፊክ ፍሰቱን ሊያሳልጡ የሚችሉ ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን የሞተረኛ ትራፊክ አባላት አስመርቋል፤ በስልጠናው ላይ 173 አባላትን ያካተተ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 16ቱ ሴቶች ሲሆኑ ኮሚሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ሞተኞችን እንዳስመረቀ ተነ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦክስ ፌዴሬሽን ከጎጆ ክሬቲቭ ሚዲያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የስፖንሰር የቦክስ ውድድር ላይ የተስተዋለው ስፖርታዊ ጨዋነት ለሌሎች አርአያ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
ሪፖርተር፡- ኮን/ል አባበል ከበደ
ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ/ም አ/አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ከጎጆ ክሬቲቪ ሚዲያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ውድድር ላይ ከልዩ ልዩ የስፖርት ክለቦች የተወጣጡ የቦክስ ስፖርተኞች ተሳትፈውበታል፡፡
በዕለቱ ውድድሩን ለመከታተል በርካታ ቁጥር ያለው የስፖርት አፍቃሪ የታደመ ሲሆን ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ መጠናቀቁ የሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች ምሳሌ እንደሆነ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ አብዱ ሰመር መሀመድ እና የአ/አ/ከተማ ቦክስ ፌዴሬሽን ም/ሃላፊ አቶ አሰፋ አብርሀ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስፖርት ማስተባበሪያ ሀላፊ ም/ኢ/ር ያረጋል ሙሉ በበኩላቸው ውድድሩ በጥሩ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አካላት ድርሻቸው እንደተወጡ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ስፖርት አፍቃሪው ለስፖርቱ ማደግ እያደረገ ያለው ቀና ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
በውድድሩ ላይ በ49 ኪ.ግ የአዲስ አበባ ፖሊሱ እንዳሻው አላዩ ከኢ/ያ ወጣቶች አካዳሚ ዳዊት ፍቃዱን፤ በ64 ኪ.ግ የአዲስ አበባ ፖሊሱ መስፍን ብሩ የማራቶን ክለቡን ተመስገን ምትኩን በማሸነፍ የወርቅ ሚዳሊያ ያጠለቁ ሲሆን በ75 ኪ.ግ ሁለቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ቦክሰኞች መክብብ ከማል እና ሰይፈ ከበደ የተገናኙ ሲሆን ሰይፈ ከበደ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡
ለህክምና የመጣችውን የ3 ልጆች እናት አስገድዶ የደፈረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር
አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ ገለፀ፡፡
ሪፖርተር፡- ዋ/ሳጅን ከድር መሀመድ
ነሀሴ 10 ቀን 2009 ዓ/ም ነው ወንጀሉ የተፈፀመው፡፡ ቦታው ደግሞ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ካለው አንድ የጤና ተቋም ውስጥ ነው፡፡
ተጠርጣሪው ተቀጥሮ ከሚሰራበት የጤና ተቋም ለህክምና የመጣችውን የ3 ልጆች እናት የጤና ምርመራ ካደረገ በኋላ የህክምናዋን ውጤት እንደምትወስድ ይቀጥራታል በቀጠሮ ቀን የተገኘችው ታካሚ የህክምናዋን ውጤት ልስጥሽ በሚል ምክንያት ቢሮ እንድትገባ ካደረገ በኋላ ድርጊቱን መፈፀሙን የጉዳዩ መርማሪ ዋ/ሳጅን አውራርስ እሱባለው ተናግረዋል፡፡
በማስረጃ የተደገፈውን የምርመራ መዝገብ ዋቢ ያደረጉት መርማሪው ይህን መሰል ህክምና ስነ-ምግባር ድርጊት ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
ሪፖርተር፡- ዋና ሳጅን ከድር መሀመድ
መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ/ም ነው ወንጀሉ የተፈጸመው ቦታው ደግሞ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም ቤ/ክ ቅጥር ግቢ ነው ፡፡
ተከሳሽ ወደ ቤተክርሰቲያኑ ቅጥር ግቢ በመግባት ከተቀመጠው ሙዳይ ምፅዋት ሳጥን የመርፌ ቁልፍ በመጠቀም 2 መቶ ብር ሲያወጣ በቦታው የነበሩ ምዕመናን ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የባልቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ተወካይ የሆኑት ኢ/ር መስፍን ምትኩ ተናግረዋል፡፡
እንደ ሀላፊው ገለፃ ተከሳሽ በተለያየ ጊዜያት በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመግባት ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት እንደሚፈፅም የምርመራ መዛግብቱንና የኋላ ታርኩን ዋቢ በማድረግ ገልፀዋል፡፡ የተከሳሽን ምርመራ መዝገብን ተጠናቆ ለውሳኔ ለዐቃቤ ህግ መቅረቡንም ተናግረዋል፡፡
በቤተክርስቲያናት ውስጥ ለአምልኮ የሚመጡ ምዕመናንን ተመሳስሎ የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለምችሉ አብያተ ክርስቲያናቱ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
‹‹ ራዕይ ሠንቀናል ለላቀ ድል ተነሳስተናል!! ››
‹‹ ራዕይ ሠንቀናል ለላቀ ድል ተነሳስተናል!! ››
በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን 10ኛዉ ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀንን ለማክበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከ3መቶ በላይ በየደረጃዉ ከሚገኙ የፖሊስ አመራሮች ጋር ጥቅምት 2 ቀን 2010 ዓ.ም በኮሚሽኑ ሠላም አዳራሽ ዉይይት አደረገ፡፡
በውይይቱ ላይ ስለ በዓሉ አከባበር እንዲሁም ስለ አዲሲቷ ኢትዮጵያ ታሪክ በዋናነት ተነስቶ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተወያዮቹም ለሠንደቀ ዓላማ ክብር ሁሌም በፅናት እንቆማለን ሲሉ አሰተያየታቸዉን ሰጥተዋል፡፡
በአ/አበባ ከተማ በተለያዩ ክ/ከተሞች ጊዜ ተወስዶ በተደረገ ሰፊ ጥናት ፖሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸው ተጠርጣሪዎች በ88 የተለያዩ የወንጀል ፈፃሚዎች ቡድን የተደራጁ 216 ግለሰቦች መሆናቸውን የገለፁት በኮሚሽኑ የኢኮኖሚና የልዩ ልዩ ወንጀሎች ዲቪዚዮን ኃላፊ የሆኑት ኮማንደር አበራ ቡሊና ናቸው፡፡
ሐምሌ 30 ቀን 2009 ዓ/ም በቢሯቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳብራሩት ጊዜ በወሰደው ጥናት ከቅሚያ ወንጀል ጀምሮ በርካታ ቁጥር ያለው የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦችና የኢትዮጵያ ብር እንዲሁም የተለያየ ደረጃ ያላቸው አደንዛዥ እፆች ከግለሰቦቹ ጋር ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዳዋለ ጨምረው ገልፀዋል፡፡
ለስራው ውጤታማነት ህብረተሰቡ መረጃ በመስጠትና ጥቆማ በማድረግ ያደረገው ትብብር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደነበረው የገለፁት ኃላፊው ፖሊስ የምርመራ መዝገብ አደራጅቶ ለሚመለከተው የፍትህ አካል ለማቅረብ በዝግጅት ላይ ነው ብለዋል፡፡
መሰል የወንጀል ድርጊቶች በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያስከትሉት ተፅእኖ ከፍተኛ በመሆኑ ፖሊስ ቀጣይነት ያለው ሰፊ ጥናቶችን በማድረግ ወንጀል ፈፃሚዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልፀው የህብረተሰቡ ትብብር በቀጣይነትም ለፖሊስ ስራ ወሳኝ በመሆኑ ትብብሩ እንዲቀጥል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል ሰበታ ሃዋስ ወረዳ ላይ በሚገኘው የደብል ተራራ ላይ የኮሚሸኑ አመራርና አባላት የችግኝ ተከላ ያካሄዱት ሐምሌ 23 ቀን 2009 ዓ.ም ነው፡፡ በዕለቱ ‹‹ ለአረንጓዴ ልማታችን ስኬታማነት ሁሌም በትጋት እንሰራለን ›› በሚል መሪ ቃል በተደረገው የችግኝ ተከላ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የአ/አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ተስፋዬ ደንደና እንደገለፁት ከ2005 ዓ.ም በፊት የተራቆተውን የደበል ተራራ መልሶ ለማልማት የኮሚሽኑ አመራርና አባላት ለተከታታይ 4 አመታት ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ስፍራው ከመልማቱ በጠጨማሪ ለአካባቢ ወጣቶች ኮሚሽኑ የለገሳቸው የንብ ቀፎ በምን ደረጃ እንዳ በጤና ጥበቃ ሚንስተር ዴታና መ/ኮሚሽነር ተስፋዩ ደንደና ተጎብኝቷል፡፡ በችግኝ ተከላው ፕሮግራም ላይ የተገኙ የፖሊስ አመራርና አባላት ከ45 ሺ ችግኞች በላይ መትከላቸውን በዕለቱ ተገልጿል፡፡
የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የከተማውን ሰላምና ፀጥታ ከማስጠበቁ በተጨማሪ በአካባቢያቸው እያደረገ ያለው የአረንጓዴ ልማት ስራውን የበለጠ ሊያጠናክር ይገባል ሲሉ የሃዋስ ወረዳ ነዋሪዎች ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል፡፡
ሃይሉ ቡናሮ ወንጀሉን የፈፀመው ግንቦት 27 ቀን 2009 ዓ/ም በአራዳ ክ/ከተማ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የአ/አበባ ቀላል ባቡር ፕሮጀክት መነሻ ፌርማታ አካባቢ ነው፡፡
ተከሳሹ በተጠቀሰው ቀን ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት በመግባት ግምታቸው 6 ሺ 3 መቶ ብር በላይ የሚያወጡ 4 የእሳት ማጥፊያዎችን ከሰረቀ በኋላ እስክ ነጋ ባቡር በመጠበቅ ላይ እያለ እንቅልፍ ወስዶት ከነንብረቱ መያዙን የፌ/ጠ/ዐ/ህግ አቶ አብርሃም አያሌው ገልፀዋል፡፡
በተከሳሹ ላይ የተደራጀውን የምርመራ መዝገብ የተመለከተው የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት በነሀሴ 27 ቀን 2009 ዓ/ም ውለው ሃይሉ ቡናሮን ጥፋተኛ በማለት በ1 አመት ከ8 ወር እስራት እንድቀጣ የወሰነበት መሆኑን የምርመራው መዝገብ ያስረዳል፡፡
መንግስታዊም ሆኑ መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ለወንጀል መፈፀም ምቹ የሆኑ ንብረቶቻቸውን በተገቢ ሁኔታ እንድጠበቁ በማድረግ ወንጀልን አስቀድመው ሊከላከሉ እንደሚገባ ሃላፊው ገልፀዋል፡፡