የቤቱን ባለቤት እና የቤት ሰራተኛዋን ገለው የዘረፋ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን ፖሊስ ገለፀ፡፡ ዋና ሳጅን እመቤት ሀብታሙ

Monday, 21 August 2017 08:38

ወንጀሉ የተፈፀመው የካቲት 14 ቀን 2009 ዓ/ም ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን በን/ስ/ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል ልዩ ቦታው ላፍቶ ባንኮች ማህበር እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ሟች አቶ ተወልደ ገ/አምላክ በመኖሪያ ቤታቸው መኝታ ክፍላቸው ውስጥ ተኝተው እያለ እንዲሁም የቤት ሰራተኛቸው ሟች ትህትና ውብሸት የተባለችው ደግሞ በሌላኛዋ መኝታ ክፍል ውስጥ ተኝተዋል፡፡

የሟች ዘመድ የሆነው ተከሳሽ በቅርቡ በሟች ቤት በእንግድነት መጥቶ ከአቶ ተወልደ ጋር እየኖረ ነበር፡፡ ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም ቤቱ ውስጥ ያሉትን ንብረቶች ካጠና በኋላ የመኖሪያ ቤቱን የበር ቁልፍ በእጁ በማድረግ ቤቱን ለመዝረፍ ከሌሎች ግብረ አበሮች ጋር በመስማማት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ሟች አቶ ተወልደ ከመኝታቸው የቅርብ ዘመዳቸው ተጠርጣሪ የሻወር ቤቱ ውሃ እየፈሰሰ ነው በሚል ምክንያት ከጠራቸው በኋላ በገጀራ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ በሌላኛው መኝታ ክፍል የተኛችውን ሟች ትህትና ውብሸትን ከተኛችበት ቀስቅሰው የተፈፀመውን ድርጊት አይታለች ለፖሊስ ትናገራለች በሚል ሰበብ በተመሳሳይ ሁኔታ እሷንም ከገደሏት በኋላ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ያገኙትን ጥሬ ገንዘብ ላፕቶፕ ሁለት ታፕለት ሞባይሎችና ካሜራ እንዲሁም የሟች አልባሳትና ጫማ በመውሰድ የመኖሪያ ቤቱን በር ዘግተው ይሰወራሉ፡፡

ሟች አቶ ተወልደን ለ2 ቀናት በአካባቢው ያጡ ጎሮቤቶች ተጠራጥረው ለዘመዶቻቸው በመደወል እንደሌሉ በመግለፃቸው ቁልፍ በማስመጣትና ለፖሊስ በመደወል የካቲት 16 ቀን 2009 ዓ/ም የመኖሪያ ቤቱ በር ሲከፈት ሞተው በመገኘታቸው ምርመራው እንደተጀመረ የነገሩን የአ/አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ምርመራ ክፍል መርማሪ ዋና ሳጅን መንግስቱ ታደሰ ናቸው፡፡

ከዝግጅት ክፍላችን ጋር ቆይታ ያደረጉት ዋና ሳጅን እንደገለፁት ወንጀሉን ማንይፈፅማል የሚለውን የክትትል ቡድኑና የምርመራ ክፍሉ በመ ቀናጀት ባደረጉት ጥረት 2ቱን ወንጀል ፈፃሚዎች በመያዝና በመመርመር ወንጀሉን እንደፈፀሙ በማመን ኢግዚቢቶች እንደተያዘባቸው ተናግረዋል፡፡

እንደ መርማሪው ገለፃ በተያዙት ተጠርጣሪዎች ላይ የምርመራ መዝገብ በማደራጀትና በማጠናቀቅ ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላካቸውን ገልፀው ያልተ ያዙትን ተጠርጣሪዎች እና ንብረት ለማስመለስ ጥረት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የሟች አቶ ተወልደ ቤተሰቦችን አግኝተን ባነጋገርንበት ወቅት ወንጀል ፈፃሚዎቹ ይያዛሉ ብለው እንዳላሰቡ ገልፀው በአጭር ጊዜ ውስጥ ማንነታቸው ታውቆ በመያዛቸው እንደተሰቱ ተናግረዋል፡፡  

Rate this item
(2 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus