ኢትዮጵያ ወደ አዲስ ምዕራፍ የምትሸጋገርበት በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታ የጋራ ግብረ-ሀይል አሰታወቀ፡፡መስቀል አደባባይ የተከናወነው ሥነ-ሥርዓት በሰላም እንዲጠናቀቅ የከተማችን ነዋሪዎች ላሳዩት ጨዋነት ለተሞላበት ቀና ትብብር ግብረሀይሉ ምስጋናውን አቅርቧል። Featured

Thursday, 07 October 2021 06:48
መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያ በአዲስ መንግስት ፣በአዲስ ተስፋ አዲስ ምዕራፍ የምትጀምርበት ቀን ነው ፡፡
የጋራ ግብረሀይሉ ከፌዴራል ፖሊስ፤ከብሔራዊ መረጃ ደህንነት፤ከመከላከያ ሰራዊትና ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር አስቀድሞ ዕቅድ በማውጣት እና ህብረተሰቡን በማሰተባበር የተከናወኑት ተግባራት ውጤት አስገኝተዋል፡፡
በዛሬው ዕለት የተከናወነው የአዲስ ምዕራፍ በዓለ-ሲመት በሰላም መጠናቀቁን የፀጥታ የጋራ ግብረሀይሉ አስታውቋል፡፡
ሥነ-ሥርዓቱ በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅም በፍፁም ሙያዊ ብቃት ኃላፊነታቸውን ለተወጡ ለመላው የፀጥታ አካላትና ለሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች የፀጥታ የጋራ ግብረ-ሀይል ከፍ ያለ ምስጋናውን በታላቅ አክብሮት ያቀርባል፡፡
Last modified on Thursday, 07 October 2021 07:23
Rate this item
(3 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus