የኢ/ፌ/ፖ/ኮ/ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የፖሊስ ኮሚሽነሮች Featured

Tuesday, 24 July 2018 15:36

37749376 2086514781597100 7220517852019687424 nየኢ/ፌ/ፖ/ኮ/ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የፖሊስ ኮሚሽነሮች እና አመራሮች በተገኙበት አዲስ አበባ ስብሰባቸውን አካሂደዋል፡፡የውይይቱ አጀዳዎች መካከል የፖሊስ ሪፎረም፤የሰራዊቱ ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም፤ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የመሳሰሉት ሲሆ‹‹ህገ መንግስታዊ ተልዕኮአችንን በብቃት በመወጣት ለህግ የበላይነት መስፈን እንተጋለን›› በሚል መሪ ቃል በሰፊው ተወያይተውበታል፡፡

የፖሊስ ተቋማዊ ህዳሴ አንገብጋቢነት እና ወቅታዊነት ምን እንደሚመስል እና ተቋሙ ከሃገሪቱ እድገት ጋር የዘመነ ፖሊስን ለመፍጠር መታደስ እንዳለበትና ህዝብ የሚፈራው ሳይሆን ህዝብ የሚያከብረው ከወንጀለኛ ጋር የማይደራደር ፖሊስ ለመፍጠር የሚያስችል የመዋቅር /ሪፎርም/በመዘርጋት ዘመናዊ የፖሊስ ሃይል ማፍራት አለብን ብለዋል፡፡

ኮምሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጅማል እንደገለጹት የጠራና ግልጽ አሰራሮችን ለመከተልና ወደ ስራ ለመግባት በሰራዊቱ የደሞዝ፡የሬሽን፤የመኖሪያ ካምፕ እና ሌሎች ከኑሮ ሁኔታዎች ጋር የሚታዩ ቸግሮች በአፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጠው አጽኖት በመስጠት ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ኮሚሽነር ጀኔራሉ አየይዘው እደተናገሩት ከምንግዜውም በላይ በፖሊስ እና በጸጥታ ሃይሉ ማህበራዊ ሁኔታ በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው እነደሚሰሩና ሪፎርሙ አሰከ አባላት ድረስ የሚወረድ አደረጃጀት አንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
# Ethiopian Federal Police Commission - ህዝብ ግንኙነት37768712 2086515894930322 4635716665391185920 n

Rate this item
(1 Vote)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus