ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ሊዘዋወር የነበረ ጥይት በሕብረተሰቡ ጥቆማ ከእነ ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
ጥይቱ የተያዘው በኮ/ቀ/ክ/ከተማ ወረዳ 3 ክልል ልዩ ቦታዉ አየር ጤና አውቶቢስ ተራ መናሃሪያ ግቢ ዉስጥ ነዉ፡፡
አንድ ግለሰብ ብዛቱ 394 ጥይት በመዳበሪያ ጠቅልሎ ከአዲስ አበባ ወደ ክልል ከተሞች ይዞ ለመሄድ ሲሞክር አየር ጤና መናኸሪያ ውሰጥ በአሽከርካሪው እና በረዳቱ በተደረገ ፍተሻ ተጠርጣሪው ከእነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በአሁን ወቅት በሃገሪቱ በተለያዩ ስፍራዎች እየተስተዋለ የመጣዉን ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ከመከላከል በተጨማሪ ሊያስከትል የሚችለዉን ጉዳት በመረዳት ህ/ሰቡ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር በመሆን እያደረገ ያለዉን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡