በርበሬነው በማለት የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጠራባቸው ነው፡፡ መሰል ወንጀሎችን በመከላከል ዙሪያ የመናኸሪያ ሰራተኞ እያደረጉት ያለው አስተዋዕፆ ሊበረታታ ይገባል ተብሏል፡፡
በወንጀሉን የተጠረጡት ግለሰቦች ታህሳስ 4 ቀን 2011 ዓ/ም ለሊት ከንጋቱ 11፡30 ሠዓት ላይ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎችን በርበሬ ነው በማለት በሁለት ማዳበሪያዎች ውስጥ አድረገው በህዝብ ማመላለሻ አውቶቢስ ለማስጫን ሲሞክሩ በጫኝና አውራጅ ስራ ላይ የተሰማሩ ተጠራጥረው ባደረጉት ፍተሻ መሳሪያዎቹን ከነተጠርጣዎቹ ይዘው ለፖሊስ ማስረከባቸውን ከአዲስ ፖሊስ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተው እያንዳንዱ ሰው ለሀገሩ ሰላም ሲል አስፈላጊውን ትብብር ሊያርግ ይገባል ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
የጉዳዩ መርማሪ ም/ ሳጅን ዳኛቸው ለገሰ እንደተናገሩት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ክልል በሚገኘው ትልቁ መናኸሪያ ተብሎ በሚጠራ ቦታ በተደጋጋሚ ጊዜ ተመሳሳይ ወንጀሎች እንደሚፈፀም አስታውሰው በአውቶቢስ ተራው ውስጥ በጫኚና አውራጅ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተሰማሩ ግለሰቦችን በተደጋጋሚ ጊዜ እጅ ከፍንጅ ይዘው ለፖሊስ ማስረከባቸው የሚበረተታ ስለሆነ ተግባሩ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡