አንዳንድ ግለሰቦች ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ

Wednesday, 12 December 2018 12:20

አንዳንድ ግለሰቦች ቅዳሜና እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በእንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውን ፖሊስ ገለፀ፡፡ ሰልፉ በከተማው አስተዳደር ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል በአንዳንድ ስፍራዎች ከፀጥታ ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ ችግሮች ሊቀረፉ ይገባል እንዲሁም የተጀመረውን የለውጥ እንቅስቃሴ እንደግፋለን የሚሉ መነሻ ሃሳቦችን ምክንያት በማድረግ ቅዳሜ ታህሳስ 6 እና እሁድ ታህሳስ 7/2011 ዓ/ም አንዳንድ ግለሰቦች በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን መረጃ እንደደረሰው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩም ይሁን በፖሊስ እውቅና የሌለው መሆኑን የኮሚሽኑ ኢንዶክተሪኔሽን እና ህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ከላከው ዜና መረዳት ተችሏል፡፡logo

ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ-መንግስታዊ መብት ቢሆንም በተጠቀሱት ቀናት ሰልፍ እናደርጋለን የሚሉ ወገኖች የሰልፉን መነሻ እና መድረሻ ፣ የሰልፉን አስተባባሪዎች ማንነትና አድራሻ እንዲሁም መሰል ተያያዥ ጉዳዮች ለሚመለከተው አካል ባለማሳወቃቸው ምክንያት አስፈላጊውን ጥበቃ ለማድረግ እንደሚቸገር ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ቅዳሜና እሁድ ሌሎች ተግባራትን ለማከናወን አስቀድሞ ፕሮግራም የያዘ ስለሆነ ሰልፍ እናደርጋለን ለሚሉ ወገኖች ጥበቃ ለማድረግ የሰው ኃይል ችግር ሊያጋጥመው እንደሚችል ኮሚሽኑ ጠቁሞ ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ ይሁን በፖሊስ ኮሚሽኑ እውቅና የሌለው መሆኑን ሰልፉን የጠሩ ወገኖች ፣ የሚመለከታቸው ሌሎች አካላት እንዲሁም ህብረተሰቡ እንዲገነዘቡለት ኮሚሽኑመልእክቱን አስተላፏል፡፡

በመጨረሻም ይህንን መልዕክት ተላልፈው ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ የሚደረግ ከሆነ በህግ አግባብ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል፡፡

Last modified on Wednesday, 12 December 2018 12:36
Rate this item
(2 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus