ህዳር 20 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ሊገባ የነበረው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሱሉልታ ኬላ ላይ በአዲስ አባበ ፖሊስ በሻለቃ አራት የወንጀል መከላከል ተወርዋሪ ሃይል አባላት እና በብሄራዊ ደህንነት ሰራተኞች 9120(ዘጠኝ ሺ አንድ መቶ ሃያ ) የክላሽ ኮቭ ጥይት እና 39600 ብር (ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ስድስት መቶ)ብር በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ህገ ወጥ የጦር መሳሪያው እና ገንዘቡ ሊያዝ የቻለው በቅድመ ህብረተሰብ ጥቆማ አማካኝነት ነው፡፡ የከተማችን አዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈንና የህግ የበላይነትንለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከህብረተሰቡና ከሚመለከተቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እያደረገ ያለው የወንጀል መከላከል ተግባር የሚበረታታ ነው፡፡ በተለይ ሰፊው የህብረተስብ ክፍል ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን አስቀድሞ በመጠቆም በህግ እንዲጠየቁ በማድረግ ረገድ ትብብሩን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡