የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ከ1ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የፅዳት ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ።
***
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የድጋፍ መርሀ ግብሩ የተካሄደው በክፍለ ከተማው ወረዳ 3 በሚገኘው መቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል ነው።
በድጋፍ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ያሲን ሁሴን እንደገለፁት የፖሊስ አመራሩና አባላቱ ከመደበኛ የህግ ማስከበርና የፀጥታ ስራ በተጨማሪ ማህበራዊ ተሳትፎ በማድረግ ካላቸው አዋጥተው ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን እያሳዩ ይገኛሉ፤ ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን በቂ ነውና በማዕከሉ አቅመ ደካሞችን በመጎብኘታችን እርካታ አግኝተናል ብለው በማዕከሉ ያሉ ወገኖች ጊዜ ጥሏቸው ተጎድተው የነበሩ አሁን ላይ ፈጣሪ በጎ አሳቢ በጎ የሆነ ሰው ዶክተር ቢንያምን አዘጋጅቶላቸው ተመልሰው እየተለወጡ ያሉ በመሆናቸው ሁሉም መሠል ድጋፎችን ሊያደርግና ሊጎበኛቸው የሚገባ ሲሆን እኛም እንደ ህዝባዊ ፖሊስነታችን ድጋፋችንን ወደ ፊትም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
የፖሊስ መምሪያው የሎጀስቲክ ዲቪዝዮን ኃላፊ ኮማንደር ዴታሞ ተማም ይህ በጎ ተግባር ለአንድ ወገን ብቻ የሚተው አይደለም አሁን ላይ በተለያዩ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዘዴዎች ዜጎች የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እያበረከቱ ይገኛሉ፤ ሆኖም መጠናከር ይኖርበታል ፖሊስም የህዝብ ልጅ ከህዝብ የተገኘ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ብቻ ሳይወሠን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ግንባር ቀደም ሆኖ ከመደበኛው የህግ ማስከበር ስራው ጎን ለጎን ድጋፉን አጠናክሮ የቀጠለበት እና ድጋፉም የዚህ ማሳያ ሲሆን ፖሊስ አሁንም የህብረተሰቡን ማህበራዊ ችግሮች ለመቅረፍ ከመደበኛ ስራው ጎን ለጎን በጎ ተግባሩን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የ8ቱ ፖሊስ ጣቢያና የመምሪያው አመራሮችና አባላት ካላቸው በማዋጣት የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች፣ የልብስና የገላ ሳሙና እንዲሁም ሶፍት በአጠቃላይ 1ሚሊየን 6ሺህ 4መቶ 60 ብር የሚገመት ድጋፍ አድርገዋል።
*
ዘገባ፡- ዋና ሣጅን አዳነ ደስታ
*
ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
“በጀግንነት መጠበቅ በሰብዓዊነት ማገልገል!”
“Protect with courage, Serve with Compassion!”