የኢፌዲሪ የመንግስት ምስረታ ፕሮግራም በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታ አካላት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቀው ወደ ሥራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

Monday, 04 October 2021 09:21
በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም በርካታ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ ስለሚመጡ እንግዶች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ መልዕክት ተላፏል፡፡
በሀገራችን የተካሄደውን 6ኛውን ብሔራዊ ምርጫ ተከትሎ የተወሰኑ ክልሎች መንግስት መመስረታቸው ይታወቃል፡፡
የተለያዩ ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ፣ ጠቅላይ ሚኒስተሮች ፣ የሀገራት ተወካዮች እንዲሁም የክልል ፕሬዝዳንቶች፣ የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ከንቲባዎች ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች እንግዶች በሚገኙበት መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም የኢፌዲሪ መንግስት ይመሰረታል፡፡
የመንግስት ምስረታው በስኬት እንዲጠናቅ እንዲሁም የኢሬቻ እና የመስቀል በአላት በሰላም እንዲከበሩ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል፡፡
ግብረ ኃይሉ እቅድ በማውጣት እና ህዝብን በማሳተፍ ባከናወናቸው ተግባራት በዓላቱ በሰላም ተከብረዋል፡፡
ህብረተሰቡ በቅረቡ የተከበሩት የኢሬቻ እና የመስቀል በዓላት በሰላም እንዲከበሩ እንዲሁም በአጠቃላይ ለፀጥታው ስራ ስኬታማት እያበረከተ ያለው አስተዋፅኦ የሚበረታታ ነው፡፡
በአላቱ በሰላም እንዲከበሩ ህዝቡ እንደሁል ጊዜው ከፀጥታ አካላት ጎን በመቆም ላደረገው ቀና ትብብር እንዲሁም ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ኃላፊናታቸው በብቃት ለተውጡ የፀጥታ አካላት አመራሮችና አባላት የጋራ ግብረ ኃይሉ ምስጋናውን እያቀረበ የመንግስት መስረታው ፕሮግራሙ በውጤት እንዲጠናቀቅ ህብረተሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን ያስተላፋል፡፡
የፕሮግራሙ ታዳሚዎች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳዮች በሚንቀሳቀሱበት ወቅት በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ ጥሪውን እያቀረበ የመንግስት ምስረታው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ፡-
1. ከሚያዚያ 27 አደባባይ ወደ ውጪ ጉዳይ ሚ/ር
2. ከአዋሬ በአዋሬ ገበያ ወደ ፓርላማ
3. ከሴቶች አደባባይ ወደ ካሳንቺስ
4. ከሴቶች አደባባይ በእንድራሴ ሆቴል ወደ ካሳንቺስ ቶታል
5. ከ22 ወደ ቅዱስ ኡራኤል እንዲሁም ከኤድናሞል በአትላስ ሆቴል ወደ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን
6. ከአትላስ ሆቴል በደሳለኝ ሆቴል ሩዋንዳ
7. ከኤምፔሪያል ሆቴል ወደ ብራስ ሆስፒታል
8. ከገርጂ ኮሪያ ሆስፒታል ውስጥ ውስጡን ወደ ብራስ ሆስፒታል
9. ከጎሮ አዲሱ መንገድ መሄጃ ወደ ብራስ ሆስፒታል
10. ከቦሌ ሚካኤል ወደ ቀለበት መንገድ እንዲሁም ከቦሌ ሚካኤል ወደ ሩዋንዳ ማዞሪያ
11. ከካዲስኮ አደባባይ ወደ ቦሌ ሚካኤል ዋናው ቀለበት መንገድ
12. ከቡልቡላ ወደ ቦሌ ሚካኤል
13. ከመስቀል ፍላውር ወደ ጎርጎሪዮስ አደባባይ
14. ከጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከጎተራ ወደ ወሎ ሰፈር አጎና ሲኒማ
15. ከጎፋ ማዛሪያ አዲሱ መንገድ መስቀለኛ ወደ ቅዱስ ቂርቆስ ቤተክርስቲያ ለገሃር
16. ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ ገንት ሆቴል እንዲሁም ከቡልጋርያ ማዞሪያ ወደ አፍሪካ ህብረት አደባባይ
17. ከልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር እንዲሁም ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ኑር ህንፃ በባልቻ መስቀለኛ ወደ አረቄ ፋብሪካ
18. ከ18 ወደ ጦር ሃይሎች 3 ቁጥር ማዞሪያ የሚወስደው ከላይም ከታችም
19. ከሞላ ማሩ ወደ ቅድስት ልደታ ቤተ-ክርስቲያን
20. ከተክለ ሃይማኖት በርበሬ በረንዳ ወደ ዲ-አፍሪክ ሆቴል
21. ከተክለ ሃይማኖት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል
22. ከአብነት ፈረሳኛ በቀድሞ 5ኛ ፖሊስ ጣቢያ ጎማ ቁጠባ ወደ ብሔራዊ ቴአትር
23. ወሎ ሰፈር፣ ኦሎምፒያ፣ መስቀል አደባባይ ብሔራዊ ቤተ- መንግስት ግቢ ገብርኤል መታጠፊያ ሸራተን አዲስ አራት ኪሎ
24. ጎርጎሪዮስ አደባባይ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ/ም ፕሮግራሙ ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ለትራፊክ ዝግ ሲሆኑ ፕሮግራሙ በሚካሄድበት መስቀል አደባባይ አካባቢ ከዛሬ መስከረም 23 ቀን 2014 ዓ/ ጀምሮ በሁለቱም አቅጣጫዎች ግራና ቀኝ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሸከርካሪን አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን የፀጥታና ደህንነት ግብረኃይል አስታውቋል፡፡
እንግዶች በአጀብ ሆነ ለልዩ ልዩ ጉዳይ በሚንቀሳቀሱበት ወቅት ህብረተሰቡ በተለይ ደግሞ አሽከርካሪዎች ቅድሚያ በመስጠት የተለመደ ትብብራቸውን እንዲያደርጉ ግብረ ኃይሉ መልዕክቱ አስተላልፏ ።
ፎቶው ዝርዝር መግለጫ የለዉም
 
Last modified on Monday, 04 October 2021 09:25
Rate this item
(1 Vote)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus