ህገ ወጥ የተሽከርካሪ ጥቁር ሽፋን (Sticker) ፈቃድ ወረቀት በሚጠቀሙ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል፡፡

Thursday, 29 October 2026 06:35

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ ህገ ወጥ የይለፍ ወረቀት (Pass) በሚጠቀሙ፣ ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ አካል ውጪ የሆነ የጥቁር ስቲከር ፈቃድ ወረቀት እንዲሁም በልየ ልዩ የደንብ መተላለፍ ጥፋቶች ውስጥ የተገኙ ሞተር ሳይክልና ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ ይገኛል፡፡ ዋና ጠቅላይ መምሪያው በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ብቻ ባደረገው ቁጥጥር አንድ ሺህ አንድ መቶ አስራ አንድ ተሽከርካሪዎች ላይ በደንቡ መሰረት ርምጃ መውሰዱን የትራፊክ ዋና መምሪያ ኃላፊው ኮማንደር አበራ ባይሳ ገልፀዋል፡፡ ኃላፊው አያይዘውም ጊዜው ያለፈበትና ፈቃድ ሰጪው አካል የማይታወቅ የስቲከር ፈቃድ ወረቀት የያዙ 899፣ 153 በተለያዩ የደንብ ጥሰቶች ውስጥ የተገኙ የሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎች እንዲሁም አፈር ጭነው መንገድ ያበላሹ 59 ተሽከርካሪዎች ላይ በትራፊክ ደንቡ መሰረት ህጋዊ ርምጃ ተወስዷልም ብለዋል፡፡ አሽከርካሪዎቹ የትራፊክ ቁጥጥርን መጣስ፣ በከተማ ክልል ከተፈቀደው የፍጥነት ወሰን በላይ ማሽከርከር፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸውና ያልታደሱ የጥቁር መስታወት ሽፋኖችን ፈቃድ ወረቀት መጠቀምና መሰል ጥፋቶችን በመፈፀማቸው የተወሰደ ርምጃ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡ አሽከርካሪዎች በከተማዋ ያለው የመንገድ ደህንነትና የትራፊክ ፍሰት ሠላማዊ እንዲሆን የድርሻቸውን እንዲወጡ ያሳሰበው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በደንብ ተላላፊዎች ላይ የሚደረገው ቁጥጥር ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፦ ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
*

ለፖሊሳዊ መረጃዎቻችን፦
በፌስቡክ :- https://www.facebook.com/Addisababapolice
በቲክቶክ ፦https://www.tiktok.com/@addisababapoliceofficial?
በቴሌግራም:- https://t.me/addispolice
በዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/AddisAbabaPoliceCommission
በትዊተር፦Twitter https://twitter.com/AddisPolice
ድረ ገጽ፦ web https://www.addispolice.gov.et/
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!
?? ??? ??
Last modified on Thursday, 29 October 2026 06:56
Rate this item
(0 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus