በኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ አማካኝነት የተዘጋጀው የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር እስኪጠናቀቅ የተወሰኑ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ፡፡
***
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 14 ቀን 2019 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ጥቅምት 15 ቀን 2019 ዓ/ም መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ያደረገ የሩጫ ውድድር ይካሄዳል፡፡
ከተማችን የምታስተናግደው የሩጫ ውድድር በሠላም እንዲጠናቀቅ መላው የፀጥታ አካላት ዝግጅታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ መግባታቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አስታውቆ፤ የሩጫው ተሳታፊዎች ፀጥታው የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተገንዝበው ወደ መሮጫ ስፍራው ሲገቡ ለፍተሻ እንዲተባበሩም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ሩጫው ተጀምሮ እስኪሚጠናቀቅ ፡-
• ከቅዱስ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኦሎምፒያ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ
• በወንጌላዊት ህንፃ ወደ ጎተራ
• ከቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን ወደ ጎተራ
• ከጎፋ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከሳር ቤት ወደ ጎፋ ማዞሪያ
• ከአፍሪካ ህብረት ወደ ብልጋሪያ
• ከትምባሆ ሞኖፖል ወደ ገነት ሆቴል
• ከጥይት ቤት ወደ ጠማማው ፎቅ
• ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ለገሃር
• ከቅድስት ልደታ ቤተ ክርስቲያን ወደ ለገሃር
• ከሰንጋ ተራ ወደ ለገሃር
• ከብሔራዊ ቴአትር ወደ ለገሃር
• ከሐራምቤ ሆቴል ወደ መስቀል
• ከቤተመንግስት ወደ መስቀል
• ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስዱ መንገዶች ነገ ከንጋቱ 11፡30 ጀምሮ ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ፡፡ በውድድሩ መስመር ግራና ቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ዋና ጠቅላይ መምሪያው አስታውቋል፡፡
*
ዘገባ፡- ም/ኢንስፔክተር ዳዊት እርገጤ
በጀግንነት መጠበቅ ፤ በሰብዓዊነት ማገልገል!
Protect with Courage, Serve with Compassion!