ፖሊስ ዜና

ዕውቅናና ማበረታቻ ተሰጠ!

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በስራ እንቅስቃሴዎቻቸው ጎልተው በመውጣት ከተጠርጣሪዎች የገንዘብ መደለያ አንቀበልም ሲሉ ለህግ በማቅረብ ለሰሩት አኩሪ ተግባር ለአመራርና ለአባላቱ የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል፡፡ መስከረም 12 እና መስከረም 22 ቀን 2011 ዓ/ም በተዘጋጀው የእውቅና አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ የተገኙት ኮሚሽነር ደግፌ በዲ የከተማዋን ነዋሪዎች የፍትህ ጥያቄ በአግባቡ ሊመልስ የሚችል የፖሊስ ኃይል ለመፍጠር ሰፊ ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረው ለተሸላሚዎቹ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ም/ኮሚሽር ዘላለም መንግስቴ በበኩላቸው መንግስት የጥቁር ገበያን ለመግታት በጀመረው ዘመቻ የኮሚሽኑ አባላት ከሁለት ሚሊየን እስከ አንድ መቶ ሺህ ብር ድረስ ከተጠርጣሪዎች የቀረበላቸው መደለያ ሳያጓጓቸው ተጠርጣሪዎችን ለህግ በማቅረባቸው የፖሊስ ተቋሙን ያኩሩ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡ በቀጣይም መሰል ማበረታቻዎች እንደሚቀጥሉ ገልፀው አዳዲስ የፖሊስ አባላትም ከዚህ አርአያነት ካለው ተግባር ብዙ ትምህርት ሊማሩ ይገባል ብለዋል፡፡
የፖሊስ ስራ በትልቅ መስዋዕትነት ውስጥ የሚገኝ መሆኑን የጠቀሱት የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ም/ኮሚሽነር ሀሰን ነጋሽ ይህ ማበረታቻ ሙያዊ ስነ ምግባራቸውን ጠብቀው ለሚሰሩ አባላትና አመራሮች ትልቅ ብርታት ነው ብለዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይ የ20ኛ ዙር የፖሊስ አባላት አቀባበል የተደረገ ሲሆን የፖሊስ አመራሩና አባላቱ ላከነወኑት ተግባር አድናቆታቸውን ገልፀው አርአያነታቸውን እንደሚከተሉም ተናግረዋል፡፡
com.shilmatcom2 shilmatshilmat 2

*********************************
መስከረም 01 ቀን 2011 ዓ/ም በግምት ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ሲሆን በቂርቆስ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ቦልጋሪያ ( የድሮ በግ ተራ ) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕድሜያቸው የ19 እና የ20 ዓመት የሆኑ እህትማማቾችን የመኪና አደጋ በማድረስ የተሰወረው የፖሊስ መኪና አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር መዋሉ ታውቋል፤ ምርመራውን በማጣራት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ሲሆን ተከሳሹ አደጋውን ካደረሰ በኋላ ላለፉት 19 ቀናት ተሰውሮበት ከነበረው ከምስራቅ ጎጃም ደንባ ወረዳ በክትትል መያዙ ታውቋል፡፡ 
ተጠርጣሪውን በህግ ቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ አድካሚ ፍለጋ ማድረጉንም ተገልጧል፡፡ ህብረተሰቡ በማህበራዊ ሚዲያዎች ከሚጻፉት ጉዳዮች ይልቅ፤ ወደ ኮሚሽኑ በመምጣት መረጃ ማግኘት የሚችል መሆኑ ተገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን 1439ኛው የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ፡፡ ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዩች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡
አዲስ አበባ የአረፋበዓል በድምቀት ከሚከበርባቸው ከተሞች አንዷ ነች፡፡ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በርካታ ቁጥር ያላቸው የእምነቱ ተከታዩች በጋራ በአዲስ አበባ ስታዲየም ሶላት ያደርጋሉ፡፡ በሶላት ወቅትም ይሁን ከዚያም በኋላ በዓሉ በሰላም እንዲያከበር ፖሊስ ኮሚሽኑ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል፡፡
በበዓሉ እለት በአዲስ አበባ ስታዲዩም እና በዙሪያው ፍተሻ መኖሩን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፍተሻ እንዲተባበር ፤ የእምነቱ ተከታዩች ለሶላት ሲመጡ የስለት መሳሪያዎችን እና ሌሎችአዋኪ ነገሮችን ይዞ ባለመምጣት የተለመደ ትብብር እንዲያደርጉ ኮሚሽኑ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡
ከዚህ ቀደም የተከበሩ ሃይማኖታዊና ብሄራዊ በዓላት በሰላም እንዲከበሩ ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር ከፍተኛ አስተዋእፆ ማበርከቱን ኮሚሽኑ አስታውሶ የዘንድሮ የአረፋ በዓል በሰላም እንዲከበር ህብረተሰቡ የተለመደውን ትብብር እንዲያደርግ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቀርቧል፡፡arefa


በአዲስ አበባ ስታዲዮም የሚደረገውን የሶላት ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የትራፊክ መጨናነቅ እንዳይፈጠር፡-
• ከቦሌ ኦሎምፒያ  ፍላሚንጎ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከኡራኤል ባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ
• ከአራት ኪሎ  ብሄራዊ ቤተ-መንግስት ወደ እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን
• ካሳንቺስብሄራዊ ቤተ-መንግስትፍልውሃ
• ከንግድ ማተሚያ ቤት ኦርማ ጋራዥ ፍልውሃ ሐራምቤ ሆቴል
• ከቴዎድሮስ አደባባይ ኢሚግሬሽን ሐራምቤ ሆቴል ስታዲዬም
• ከጎማ ቁጠባ ብሄራዊ ቲያትር ስታዲዬም
• ከሰንጋ ተራ በድሉ ህንፃ  ስታዲዬም
• ከሰንጋ ተራ በለገሃር ስታዲዬም
• ከሜክሲካ አደባባይ በለገሃር ስታዲዬም
• በቂርቆስ አዲሱ መንገድበለገሃር ስታዲዬም
• በሐራምቤ ሆቴል  ጋንዲ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ
• ከጎተራ  በአራተኛ ክፍለ ጦር ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ለጊዜው ለተሽከርካሪ ዝግ ሲሆኑ
ከቦሌ ወደ ኣራት ኪሎ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
በኡራኤል በካሳንቺስ አራት ኪሎ
ከመገናኛ ወደ ጦር ኃይሎች መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
በኡራኤል  ካሳንቺስ ታላቁ ቤተ-መንግስት  እሪበከንቱ ቴዎድሮስ አደባባይ ኤክስትሪም ሆቴል  ተክለ ሀይማኖት  ጣር ሀይሎች
ከሳሪስ አቅጣጫ ወደ አራት ኪሎ እና ፒያሳ መሄድ የሚፈልጉ አሽከርካሪዎች
ጎተራ  ወሎ ሰፈር  አትላስ ሆቴል  ኡራኤል  ካሳንቺስ  አራት ኪሎ ያሉ መንገዶችን በአማራጭነት መጠቀም እንደሚችሉ ኮሚሽኑ ገልፆል፡፡
ከዛሬ ነሃሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ማታ ጀምሮ የሶላቱ ስነ-ስርዓት ተጀምሮ እስከሚጠናቅ ድረስ በስታዲዬም ዙሪያ እና አካባቢው በግራና ቀኝ ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡
ህብረተሰቡ ለጸጥታ አጠራጣሪ የሆኑ ነገሮች ሲያጋጥሙት ይሁን የፖሊስ አገልግሎትን ለማግኘት ከፈለገ በስልክ ቁጥሮች-
• 011-5-52-63-03
• 011-5-52-40-77
• 0115-52-63-02
• 011-1-11-01-11
ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 እና 987 መጠቀም እንደሚችል ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡ በመጨረሻም ኮሚሽኑ ለመላው የእምነቱ ተከታዩች በዓሉ የሰላም የደስታ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ገልፆል፡፡

pol-traff2pol-traff
የዓለም ባንክ በ175 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ 275 የሞተር ሳይክሎችን እና 32 ተሽከርካሪዎችን ግዢ በመፈፀም ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አበርክቷል፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ዶ/ር ኢ/ር ሠለሞን ኪዳኔ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ዘላለም መንግስቴ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ ከተማችን አዲስ አበባ ከመንገድ ትራፊክ አደጋ የፀዳች ትሆን ዘንድ ተግቶ መስራት እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

37749376 2086514781597100 7220517852019687424 nየኢ/ፌ/ፖ/ኮ/ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የፖሊስ ኮሚሽነሮች እና አመራሮች በተገኙበት አዲስ አበባ ስብሰባቸውን አካሂደዋል፡፡የውይይቱ አጀዳዎች መካከል የፖሊስ ሪፎረም፤የሰራዊቱ ደመወዝ እና ጥቅማ ጥቅም፤ወቅታዊ ሁኔታን በተመለከተ የመሳሰሉት ሲሆ‹‹ህገ መንግስታዊ ተልዕኮአችንን በብቃት በመወጣት ለህግ የበላይነት መስፈን እንተጋለን›› በሚል መሪ ቃል በሰፊው ተወያይተውበታል፡፡

የፖሊስ ተቋማዊ ህዳሴ አንገብጋቢነት እና ወቅታዊነት ምን እንደሚመስል እና ተቋሙ ከሃገሪቱ እድገት ጋር የዘመነ ፖሊስን ለመፍጠር መታደስ እንዳለበትና ህዝብ የሚፈራው ሳይሆን ህዝብ የሚያከብረው ከወንጀለኛ ጋር የማይደራደር ፖሊስ ለመፍጠር የሚያስችል የመዋቅር /ሪፎርም/በመዘርጋት ዘመናዊ የፖሊስ ሃይል ማፍራት አለብን ብለዋል፡፡

ኮምሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጅማል እንደገለጹት የጠራና ግልጽ አሰራሮችን ለመከተልና ወደ ስራ ለመግባት በሰራዊቱ የደሞዝ፡የሬሽን፤የመኖሪያ ካምፕ እና ሌሎች ከኑሮ ሁኔታዎች ጋር የሚታዩ ቸግሮች በአፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጠው አጽኖት በመስጠት ማብራሪ ሰጥተዋል፡፡ኮሚሽነር ጀኔራሉ አየይዘው እደተናገሩት ከምንግዜውም በላይ በፖሊስ እና በጸጥታ ሃይሉ ማህበራዊ ሁኔታ በተመለከተ ትኩረት ሰጥተው እነደሚሰሩና ሪፎርሙ አሰከ አባላት ድረስ የሚወረድ አደረጃጀት አንደሚደረግ ገልጸዋል፡፡
# Ethiopian Federal Police Commission - ህዝብ ግንኙነት37768712 2086515894930322 4635716665391185920 n

37017694 2074559512792627 7888051646373036032 n37048489 2074559696125942 6171986743017865216 n
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የቦክስ ቡድን የኢትዮጵያ ቦክስ ፌደሬሽን የሚያዘጋጀውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልቦች ሻምፒዮና ውድድር ላይ ተካፋይ በመሆን አራት ዙር በሴት 6 የወርቅ፣ 3 የብር እና 6 ነሐስ በአጠቃላይ በ15 ሜዳሊያዎች 30 ነጥብ በማምጣት የዓመቱ አሸናፊ በመሆን ውድድሩን በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ በተመሳሳይ በወንዶች ደግሞ በ38 ነጥብ የሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቋል፡፡

ሴት ሞተረኛ ትራፊክ …!
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ አደጋን በመከላከልና የትራፊክ ፍሰቱን ሊያሳልጡ የሚችሉ ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን የሞተረኛ ትራፊክ አባላት አስመርቋል፤ በስልጠናው ላይ 173 አባላትን ያካተተ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 16ቱ ሴቶች ሲሆኑ ኮሚሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ሞተኞችን እንዳስመረቀ ተነግሯል፤ ም/ኮሚሽነር ተስፋዬ ደንደና የመንገድ ትራፊክ አደጋን መከላከል ዋንኛ ተግባር ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡  23658675 1948988098683103 8533589116866215895 n23658628 1948987512016495 2341851417892640062 n

23659246 1948987485349831 6962084995295309873 n23755539 1948987648683148 2415551980465167040 nሴት ሞተረኛ ትራፊክ …!
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የመንገድ ትራፊክ አደጋን በመከላከልና የትራፊክ ፍሰቱን ሊያሳልጡ የሚችሉ ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን የሞተረኛ ትራፊክ አባላት አስመርቋል፤ በስልጠናው ላይ 173 አባላትን ያካተተ ሲሆን ከዚሁ ውስጥ 16ቱ ሴቶች ሲሆኑ ኮሚሽኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ሞተኞችን እንዳስመረቀ ተነ23622126 1948987332016513 7916339424842771036 n

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦክስ ፌዴሬሽን ከጎጆ ክሬቲቭ ሚዲያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የስፖንሰር የቦክስ ውድድር ላይ የተስተዋለው ስፖርታዊ ጨዋነት ለሌሎች አርአያ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
ሪፖርተር፡- ኮን/ል አባበል ከበደ

rsz ai4a1051ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ/ም አ/አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ከጎጆ ክሬቲቪ ሚዲያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ውድድር ላይ ከልዩ ልዩ የስፖርት ክለቦች የተወጣጡ የቦክስ ስፖርተኞች ተሳትፈውበታል፡፡
በዕለቱ ውድድሩን ለመከታተል በርካታ ቁጥር ያለው የስፖርት አፍቃሪ የታደመ ሲሆን ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ መጠናቀቁ የሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች ምሳሌ እንደሆነ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ አብዱ ሰመር መሀመድ እና የአ/አ/ከተማ ቦክስ ፌዴሬሽን ም/ሃላፊ አቶ አሰፋ አብርሀ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስፖርት ማስተባበሪያ ሀላፊ ም/ኢ/ር ያረጋል ሙሉ በበኩላቸው ውድድሩ በጥሩ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አካላት ድርሻቸው እንደተወጡ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ስፖርት አፍቃሪው ለስፖርቱ ማደግ እያደረገ ያለው ቀና ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
በውድድሩ ላይ በ49 ኪ.ግ የአዲስ አበባ ፖሊሱ እንዳሻው አላዩ ከኢ/ያ ወጣቶች አካዳሚ ዳዊት ፍቃዱን፤ በ64 ኪ.ግ የአዲስ አበባ ፖሊሱ መስፍን ብሩ የማራቶን ክለቡን ተመስገን ምትኩን በማሸነፍ የወርቅ ሚዳሊያ ያጠለቁ ሲሆን በ75 ኪ.ግ ሁለቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ቦክሰኞች መክብብ ከማል እና ሰይፈ ከበደ የተገናኙ ሲሆን ሰይፈ ከበደ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡rsz ai4a1031rsz ai4a1067

 

rsz ddለህክምና የመጣችውን የ3 ልጆች እናት አስገድዶ የደፈረውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር

አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ፖሊስ ገለፀ፡፡
ሪፖርተር፡- ዋ/ሳጅን ከድር መሀመድ

ነሀሴ 10 ቀን 2009 ዓ/ም ነው ወንጀሉ የተፈፀመው፡፡ ቦታው ደግሞ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 7 ካለው አንድ የጤና ተቋም ውስጥ ነው፡፡
ተጠርጣሪው ተቀጥሮ ከሚሰራበት የጤና ተቋም ለህክምና የመጣችውን የ3 ልጆች እናት የጤና ምርመራ ካደረገ በኋላ የህክምናዋን ውጤት እንደምትወስድ ይቀጥራታል በቀጠሮ ቀን የተገኘችው ታካሚ የህክምናዋን ውጤት ልስጥሽ በሚል ምክንያት ቢሮ እንድትገባ ካደረገ በኋላ ድርጊቱን መፈፀሙን የጉዳዩ መርማሪ ዋ/ሳጅን አውራርስ እሱባለው ተናግረዋል፡፡
በማስረጃ የተደገፈውን የምርመራ መዝገብ ዋቢ ያደረጉት መርማሪው ይህን መሰል ህክምና ስነ-ምግባር ድርጊት ለመከላከል ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፡

 

ሪፖርተር፡- ዋና ሳጅን ከድር መሀመድ

images 4 

 

 

መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ/ም ነው ወንጀሉ የተፈጸመው ቦታው ደግሞ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም ቤ/ክ ቅጥር ግቢ ነው ፡፡

 

ተከሳሽ ወደ ቤተክርሰቲያኑ ቅጥር ግቢ በመግባት ከተቀመጠው ሙዳይ ምፅዋት ሳጥን የመርፌ ቁልፍ በመጠቀም 2 መቶ ብር ሲያወጣ በቦታው የነበሩ ምዕመናን ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የባልቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ተወካይ የሆኑት ኢ/ር መስፍን ምትኩ ተናግረዋል፡፡

 

እንደ ሀላፊው ገለፃ ተከሳሽ በተለያየ ጊዜያት በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመግባት ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት እንደሚፈፅም የምርመራ መዛግብቱንና የኋላ ታርኩን ዋቢ በማድረግ ገልፀዋል፡፡ የተከሳሽን ምርመራ መዝገብን ተጠናቆ ለውሳኔ ለዐቃቤ ህግ መቅረቡንም ተናግረዋል፡፡

 

በቤተክርስቲያናት ውስጥ ለአምልኮ የሚመጡ ምዕመናንን ተመሳስሎ የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለምችሉ አብያተ ክርስቲያናቱ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

 

Page 1 of 2

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus