የቦክስ ውድድር ላይ የተስተዋለው ስፖርታዊ ጨዋነት

Wednesday, 01 November 2017 11:30

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቦክስ ፌዴሬሽን ከጎጆ ክሬቲቭ ሚዲያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው የስፖንሰር የቦክስ ውድድር ላይ የተስተዋለው ስፖርታዊ ጨዋነት ለሌሎች አርአያ እንደሆነ ተገለፀ፡፡
ሪፖርተር፡- ኮን/ል አባበል ከበደ

rsz ai4a1051ጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ/ም አ/አበባ ቦክስ ፌዴሬሽን ከጎጆ ክሬቲቪ ሚዲያ ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ውድድር ላይ ከልዩ ልዩ የስፖርት ክለቦች የተወጣጡ የቦክስ ስፖርተኞች ተሳትፈውበታል፡፡
በዕለቱ ውድድሩን ለመከታተል በርካታ ቁጥር ያለው የስፖርት አፍቃሪ የታደመ ሲሆን ውድድሩ ስፖርታዊ ጨዋነት በተላበሰ መልኩ መጠናቀቁ የሌሎች ስፖርታዊ ውድድሮች ምሳሌ እንደሆነ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አቶ አብዱ ሰመር መሀመድ እና የአ/አ/ከተማ ቦክስ ፌዴሬሽን ም/ሃላፊ አቶ አሰፋ አብርሀ ገልፀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስፖርት ማስተባበሪያ ሀላፊ ም/ኢ/ር ያረጋል ሙሉ በበኩላቸው ውድድሩ በጥሩ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የሚመለከታቸው አካላት ድርሻቸው እንደተወጡ ተናግረዋል፡፡ በተለይ ስፖርት አፍቃሪው ለስፖርቱ ማደግ እያደረገ ያለው ቀና ትብብር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡
በውድድሩ ላይ በ49 ኪ.ግ የአዲስ አበባ ፖሊሱ እንዳሻው አላዩ ከኢ/ያ ወጣቶች አካዳሚ ዳዊት ፍቃዱን፤ በ64 ኪ.ግ የአዲስ አበባ ፖሊሱ መስፍን ብሩ የማራቶን ክለቡን ተመስገን ምትኩን በማሸነፍ የወርቅ ሚዳሊያ ያጠለቁ ሲሆን በ75 ኪ.ግ ሁለቱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ቦክሰኞች መክብብ ከማል እና ሰይፈ ከበደ የተገናኙ ሲሆን ሰይፈ ከበደ አሸናፊ መሆን ችሏል፡፡rsz ai4a1031rsz ai4a1067

 

Last modified on Wednesday, 01 November 2017 12:21
Rate this item
(1 Vote)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

አሽከርክር ረጋ ብለህ

ፎቶዎች

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus