በተለያዩ ቤተክርስቲያናት በመግባት ከሙዳየ ምፅዋት ውስጥ ገንዘብ ሲሰርቅ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ዋለ

Wednesday, 01 November 2017 11:17

ሪፖርተር፡- ዋና ሳጅን ከድር መሀመድ

images 4 

 

 

መስከረም 1 ቀን 2010 ዓ/ም ነው ወንጀሉ የተፈጸመው ቦታው ደግሞ በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ማህደረ ስብሐት ቅድስት ልደታ ማርያም ቤ/ክ ቅጥር ግቢ ነው ፡፡

 

ተከሳሽ ወደ ቤተክርሰቲያኑ ቅጥር ግቢ በመግባት ከተቀመጠው ሙዳይ ምፅዋት ሳጥን የመርፌ ቁልፍ በመጠቀም 2 መቶ ብር ሲያወጣ በቦታው የነበሩ ምዕመናን ለፖሊስ በሰጡት ጥቆማ በቁጥጥር ስር እንደዋለ የባልቻ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል ምርመራ ማስተባበሪያ ተወካይ የሆኑት ኢ/ር መስፍን ምትኩ ተናግረዋል፡፡

 

እንደ ሀላፊው ገለፃ ተከሳሽ በተለያየ ጊዜያት በተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በመግባት ተመሳሳይ የወንጀል ድርጊት እንደሚፈፅም የምርመራ መዛግብቱንና የኋላ ታርኩን ዋቢ በማድረግ ገልፀዋል፡፡ የተከሳሽን ምርመራ መዝገብን ተጠናቆ ለውሳኔ ለዐቃቤ ህግ መቅረቡንም ተናግረዋል፡፡

 

በቤተክርስቲያናት ውስጥ ለአምልኮ የሚመጡ ምዕመናንን ተመሳስሎ የወንጀል ድርጊት የሚፈፅሙ ግለሰቦች ሊኖሩ ስለምችሉ አብያተ ክርስቲያናቱ ተገቢውን ጥበቃ እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ 

 

Last modified on Wednesday, 01 November 2017 11:49
Rate this item
(2 votes)

Leave a comment

Make sure you enter all the required information, indicated by an asterisk (*). HTML code is not allowed.

የቪድዮ ክምችት

ቪድዮዎች

ፎቶዎች

በብዛት የታየ ቪድዮ

Social Media

fbtwitteryoutubegoogleplus